ዜናዎች

#አሳዛኝ ዜና ዕረፍት

 

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ጅማ ላይ ተሳታፊው እንጅባራ ከተማ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጨዋች ተስፋፅዮን ፋንቱ (ደሮ) ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡

አምና በኢትዮ ኤሌክትሪክ በትልቅ ደረጃ መጫወት የቻለው አማካዮ በዘንድሮ የውድድር ዓመት እንጅባራ ከተማን በመቀላቀል በጨዋታ ላይ እያለ ባጋጠው የጭንቅላት ግጭት አደጋ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል።

ተስፋፅዮን ፋንቱ ሥርዓተ ቀብር በነገው እለት በሐዋሳ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ኢትዮ-ኪክ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛል!