ዜናዎች

# የሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት ዛሬ ይዘጋል!

👇የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ የ2015 ዓ.ም አጋማሽ የተጫዋቾች ዝውውር ከታህሳስ 18/2015 (December 27) ጀምሮ እስከ ጥር 18/2015 (January 26) ድረስ ለአንድ ወር ቆይቶ ዛሬ የሚዘጋ ይሆናል።
በዘንድሮው የሁለተኛ ዙር የዝውውር እንቅስቃሴ ላይ ክለቦች ብዙም ተሳትፎ ያላደረጉበት ነበር ማለት ይቻላል ።
በአንፃሩ የዝውውር መሥኮቱ ዛሬ በይፋ ከመዘጋቱ በፊት ተጨዋቾች ያስፈረሙና በስምምንት የተለያዩ ክለቦች ታይተዋል።
#ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንደተጠበቀው ያልሆነው ፋሲል ከነማ ለውጦችን በማድረግ በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ ለመቅረብ ቡድኑን ለማጠናከር ዝውውሮችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የመስመር አጥቂ ቦታ ተጫዋች የሆነውን ዱላ ሙላቱን ለአንድ አመት በሚያቆይ ውል አስፈርሟል::
#ቅዱስ ጊዮርጊስ
ለአራት ዓመት ከፈረሰኞቹ ጋር የቆየው የመሃል ተከላካዩ ደስታ ደሙ በዛሬው እለት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡
#ለገጣፎ ለገዳዲ
# የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለው ለገጣፎ ለገዳዲ በዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ከሀዲያ ሆሳዕና ኤሊያስ አታሮ እና የመስመር ተከላካዮን ተስፋዬ ነጋሽ አስፈርሟል።
መረጃ
👇
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-