From Abdu Muhammed
በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል የፌዴሬሽኑ ም/ል ፕሬዝደንት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋዩ አቶ ተፈራ ሞላ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ ሳራ ሃሰን ፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ ፣ አትሌት መሠለች መልካሙና ዶ/ር ተስፋዬ አስገዶም እንዲሁም የጽ/ቤት ተወካዩ አቶ ዮሐንስ እንግዳ ፣ አቶ አሠፋ በቀለ ፣ አቶ አስፋው ዳኜ ፣ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ፣ ዶ/ር አያሌው ጥላሁን እንዲሁም አቶ ግርማ በቀለ የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት በመሆን የትግራይ ክልል ተወላጅ አትሌቶችን በመያዝ መነሻውን ከቦሌ አየር መንገድ ያረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 8102 መዳረሻውን መቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያውን ከቀኑ 6:10 ላይ አድርጓል።
በአየር መንገዱ ሲደርሱም ከልጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው ጋር ለሁለት አመታት ሳይገናኙ የከረሙ እና ናፍቆት የተጫናቸው ወላጆች ልጆቻቸውን በሰላም ሲያገኙ ያሳዩት ፈገግታ ፣ ከአይናቸው የሚፈሰው የደስታ እምባ ስሜቱ ልዩ ነበር።
በስፍራው ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ፣ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ የአለም ፀጋይ እና ሌሎች ባለስልጣናትም በአየር መንገዱ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገዋል።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንትና በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተመራው ልዑካን ቡድን መቐለ ሲደርሱና ከቤተሰብ ጋር ሲገናኙ የነበረው የኢትዮዽያዊያን የጀግኞች አትሌቶች የደስታ እንዲሁም የወላጅ እናቱን ህልፈተ ህይወት የተረዳው የአትሌት ለተሰንበት ግደይ ዋና አሰልጣኝ ሀይሌ እያሱ የሐዘኑ ስሜት በጣም ከባድ ነበረ።
በመቀጠልም ጉዞው ወደ ደስታ ሆቴል ሲሆን በስፍራውም የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕከላዊ ዕዝ አባሉ አቶ ጌታቸው ረዳ እና የክልሉ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ገብሩ ገብራይ በሆቴሉ በመገኘት ልዑካን ቡድኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀላቅለዋል።
መረጃ
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
ድረ ገጻችንን :-
መረጃ