ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወጣት አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋሮጦ የሰሜን አሜሪካውን ክለብ ተቀላቅሏል !

 

በስዊዘርላንድ ዋናው ሱፐር ሊግ ለኤፍ ሲ ሉጋኖ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር እና ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ያለፉትን የውድድር ወራቶች አድናቆት ያተረፈው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ ቀጣዮን የፈረንጆቹ 2023 ወደ አሜሪካ በመጓዝ በአሜሪካ Major League Soccer (MLS) ለቺካጎ ፋየር ለመጫወት መስማማቱን ክለቡ በድህረ ገፁ ትላንት ይፋ አድርጓል።

በፍጥነቱ እንዲሁም በተለየ የኳስ ጥበቡ የተለየ ችሎታ ያለው የ23 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ
ቀጣዪን የ2023 የውድድር ዘመን ለአሜሪካው ቺካጎ ፋየር በውሰት የሚጫወትም ይሆናል።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አዲሱ የማረን የአሜሪካው ቺካጎ ፋየር ክለብ እና የስዊዙ ኤፍ ሲ ሉጋኖ “እህት ክለቦች መሆናቸው ሲሰማ የሁለቱም ክለቦች ባለቤት ደግሞ አሜሪካዊው ቢልዬነር ጆ ማንስዌቶ መሆኑ ተሰምቷል።

እንደሚታወሰው የማረን ሀይለስላሴ ታናሽ ወንድሙ ቅዱስ ሀይለስላሴ እንደታላቅ ወንድሙ በኤፍ ሲ ዙሪክ ክለብ በመጫወት ላይ ይገኛል ።