የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው እና ለፈረሰኞቹን በ2013 ዋና ከረዳት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ቦታ ተሰጥቷቸው የነበሩት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ወደ ሳውዲ በማቅናት በአፍሪካ ውጤታማ አሰልጣኝ ለሆነው ሌላኛው የሀገራቸው ዜጋ አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ ምክትል አሰልጣኝ መሆናቸው ተዘግቧል።
መረጃዎች ይፋ እንዳደረጉት የቅድስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ በሳውዲ አንደኛ ዲቪዚዮን አል አህሊ ስፖርት ክለብ አዲሱ ረዳት አሰልጣኝ በይፋም ተረክበዋል፡፡
በቅርቡ ከግቡፁ ኃያል ክለብ አል ሃህሊ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ሳውዲ ያመራው እና በአፍሪካ ከታላላቅ አሰልጣኞች አንዱ የሆነው አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ በሳውዲ ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የሆነውን ክለብ ከተረከበ በኋላ የአፍሪካ ውጤማነቱ በሳውዲ ሊግም ሊታይ እንደሚችልም መረጃዎች ገልፀዋል።
የቀድም የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስን ቀደም ብሎ ለደቡብ አፍሪካ ክለቦች ሳንተንስ ፣አያክስ ኬፕታውን ፣ፍሪ ስቴት ስታርስ ፣ማሪትዝበርግ ዩናይትድ ፣ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ክለቦች ገር በአሰልጣኝነት ጋር በተለያዩ የስራ ዘርፎች በማሰልጠን ሰፊ ልምድ ማካበ ተዘግባል።