ዜናዎች

በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው ኢትዮጵያዊው ሽመልስ በቀለ ሌላኛው የግብፅ ክለብ ለመጫወት ዛሬ ፊርማውን አኑሯል!

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ በመሣተፍ ታሪካዊ ተጨዋቾች ከሆኑት አንዱ እና በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ላለፉት  ዓመታት ስኬታማ ጊዜ በማሳለፍ  ብቸኛው ኢትዮጵያዊያዊ ተጨዋቾች የሆነው ሽመልስ በቀለ ዛሬ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ሸመልስ በቀለ በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ባለፉት ዓመታት በመጫወት ስኬታማ ጊዜን ማሰለፉ ይታወሳል።

ሽመልስ በግብፅ ሊግ በ 5 ዓመት የፔትሮጂት ክለብ ቆዬታው በ123 ጨዋታዎች 29 ጎሎች አስቆጥሯል። በኃላም ለሁለት አመት በምስር አልማካስ ቆዬታ አድርጎ በ60 ጨዋታዎች 16 ጎሎች በማስቆጠር እንዲሁ ለክለቡ ስኬታማ ጊዜም አሳልፏል። በኃላም  በዓመቱ  በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ12ኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ሌላኛውን የሊጉን ተወዳዳሪ ኤል ጎናን በመቀላቀል የግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ረጅም ጊዜ በመጫወት ብቸኛው ኢትዮዽያዊ ሆኗል።

 

ሽመልስ በቀለ በዛሬው ዕለት ደግሞ በቀጣይ የውድድር ዓመት ከ ENPPI Club  ጋር ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል። Ò

 

One thought on “በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው ኢትዮጵያዊው ሽመልስ በቀለ ሌላኛው የግብፅ ክለብ ለመጫወት ዛሬ ፊርማውን አኑሯል!

Comments are closed.