የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ በአሜሪካ የልብ ማህበር በኢትዮጵያ አማካኝነት ለህክምና ባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው። ለአስራ ስድስቱ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የህክምና ባለሙያ እና ወጌሻዎች ለአንድ ቀን የሚሰጠው ስልጠና ባለሙያዎቹ ለውድድር በሚገኙበት ባህር ዳር ከተማ ይከናወናል።
ቅዳሜ መስከረም 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው መርሃ ግብር በተለይም በእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የሚከሰቱ የልብና ተያያዥ ድንገተኛ አደጋዎችን መለየትና ማከም ላይ ያተኮረ የስራ ላይ ስልጠና ነው። በአጠቃላይም በሙያው እውቀትና ልምዱ ባላቸው ባለሙያዎች በንድፈ ሃሳብና በተግባር ልምምድ የሚደገፍ እንደሚሰጥ የአክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል።
በቴሌግራም :-
https://t.me/Ethio_Kickoff
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick
🔛ድረ ገጻችንን :-