ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

#ኤርትራ በኢትዮዽያ ከሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ራሷን አግልላለች !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 9/2015 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በስምንት ሀገራት መካከል ከሚካሄደው ከ17ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ኤርትራ ሪሷን አግላለች ።

ከኢትዮጵያ ጋር በአንድ ምድብ የተደለደለችው ጎረቤት ሀገር ኤርትራ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል።

የታዳጊዎች ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሀገር ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላ የነበረችው ከኤርትራ በተጨማሪ በምድብ ሁለት የተደለደለችው ሩዋንዳ ራሷን ቀደም ብላ ማግለሏ ይታወቃል።

የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድናን ዝግጅት  ቀደም ብሎ ጀምሮ ጠንከር ባለ መልኩ ማድረጉን ቀጥሏል።