በመዲናዋ አዲስ አበባ የሚገኙ ክለቦች የሚሳተፉበት እና በመካሄድ ላይ የሚገኘው የ16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች መደረጋቸው ይታወሳል።
በተለይም ለረጅም ወራቶች በአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት ምክንያት በቨገር ደርቢ በአዲስ አበባ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ የሰነበቱት ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ጨዋታ በአዲስ አበባ ዋንጫ በደጋፊያቸው ፊት በአበበ ቢቂላ ለመገናኘት ችለዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከመደረጉ በፊት
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የመክፈቻ ንግግር አድርገው ለሁለቱም ክለቦች 10 ሚሊዮን ብር በድምሩ ሀያ ሚሊዮን ብር ከተማው ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል ።
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸውም ይህንኑ በድጋሚ ብለዋል “የከተማ አስተዳደራ ስፖርትን ለማጠናከር እየወሰዳቸው ካሉ ርምጃዎች መሃከል፣ በዛሬው እለት ለከተማችን አዲስ አበባ መለያና ኩራት ለሆኑት ሁለቱ የከተማችን ክለቦች – ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብና ለኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው ያደረግነው የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተጠቃሽ ነው” ብለዋል፡፡
በአንፃሩ ከከንቲባዋ ይህንን ድጋፍ ማድረጉን ተከትሎ ሌላኛው የመዲናዋ ክለብ መቻል እና ኤልፖ ቅሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን በማሰማት መቻል ራሱን ከአዲስ አበባ ውድድሩ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
እግርኳስ ክለቡ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ደረጀ መንግስቱ እንዳስታወቀት አኛም የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ እንደመሆናችን እና ለአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜ እንደመድረሳችን የከተማ አስተዳደሩ ከሌሎቹ መለየቱ አግባብ አይደለም ለዚህም ቅሬታችንን ለከተማ አስተዳደሩ አስገብናል ምላሽ ካልተሰጠን በፍፃሜው ውድድር ያለመካፈል አቋም ድረስ ይዘናል ብለዋል ።
በተያያዘ ዘንድሮ ወደ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው የኤልፖ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክለቡ አባላት አስተዳደሩ የከተማዋን ክለቦች ለይቶ ለሁለቱ ክለቦች ብቻ ሽልማት ማድረጉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።