ቀጥታ ዜናዎች

ዳዋ ሁጤሳ እና ሐብታሙ ታደሰ 500 ካ.ሜ ቦታ ፣ የወርቅ እና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተላቸው !

ዛሬ በምዕራብ ጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ከተማ ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዳዋ ሆጤሳ እና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የሀድያ በአሁን ሰዓት ለባህርዳር ከተማ ለፈረመው ሐብታሙ ታደሰ ከስኬታማነታቸው ባሻገር ለሀገራችን እግር ኳስ እንዲሁም ለዞኑ ወጣቶች መልካም ዓርያ በመሆናቸው አባ ገዳ እና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ ደማቅ አቀባበል እና የማበረታቻ ሽልማትለእያንዳንዳቸውም የ 500 ካ.ሜ ቦታ ፣ የወርቅ እና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተላቸው።
በተጨማሪ 5 ከቡሌ ሆራ ከተማ ለተገኙ እና ለተለያዩ የሀገራችን በብሔራዊ ሊግ ክለቦች ለሚጫወቱ ተጨዋቾችም የምስጋና እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ምንጭ ፦ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ#ቲክቫ ስፖርት

One thought on “ዳዋ ሁጤሳ እና ሐብታሙ ታደሰ 500 ካ.ሜ ቦታ ፣ የወርቅ እና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተላቸው !

Comments are closed.