ቀጥታ ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-2 አዳማ ከተማ

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ የሊጉን የጎል ድርቀት የከፈተ ሲሆን በአጠቃላይ በጨዋታው ስድስት ጎሎች ተቆጠረዋል። እስካሁን በባህርዳር ስታዲየም ከተደረጉት አራት ጨዋታዎች ከተቆጠሩት 8 ጎሎች ስድስቱ በዚህ ጨዋታ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 4 ለ 2 ባሸነፈበትጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጎል የሚሆኑ አጋጣሚዎች እና በቡድኖቹ እንቅስቃሴም ክስተቶችም ተስተውለዋል።