ዜናዎች

“እዚህ ትልቅ መድረክ ላይ በመመረጤ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል”-አማኑኤል ዮሐንስ

 

የመሀል ሜዳ ሞተሩ አማኑኤል ዮሐንስ

የዋልያዎቹ የመሀል ሜዳው እስትንፋስ እና የመሀል ሜዳ ሞተሩ አማኑኤል ዮሐንስ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የጨዋታው ኮከብ በመባል ከካፍ ሽልማት ማግኘቱ ይታወሳል።

አማኑኤል በካፍ ቴክኒካል ኮሚቴ በምድብ ጨዋታዎች ከምርጥ 11 ተጫዋቾች ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል በዕጩነት የቀረበ ብቸኛ ተጫዋች እንደነበር ይታወሳል።

የዋልያዎቹ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማኑኤል ዮሃንስ ዛሬ ካፍ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በአፍሪካ ዋንጫ እስካሁን በተደረጉት ጨዋታዎች በርካታ ዒላማቸውን የጠበቁ ኳሶችን በማቀበል በ147 ኢላማቸውን የጠበቁ ኳሶች 4ተኛ ደረጃ የተሳኩ የኳስ ቅብብሎችን አድርጓል። በተጨማሪም አማኑኤል በካሜሩኑ የአፍረካ ዋንጫ በ93.3% ኳስ በማቀበል ስኬቱም ቀዳሚው ተጫዋች ለመሆን በቅቷል።

ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፍራው የደረሰ እና በውድድሩ ካደረጋቸው 3 ጨዋታዎች በሁለቱ በመሸነፍ እና በአንድ ጨዋታ አቻ በመውጣት ከውድድሩ በመጀመሪያ የተሰናበተ ቡድን እንደነበረ ይታወቃል ።

በአንፃሩ የዋልያዎቹ አማካይ አማኑኤል ዮሐንስ በሶስቱም የምድቡ ጨዋታዎች ሙሉ ደቂቃዎችን ተሰልፎ መጫወት የቻለ ብቸኛ አማካይ እና ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ ነጥብ ስናገኝ የጨዋታው ኮከብ እንደነበረ ይታወሳል።

የዋልያዎቹ የመሀልሜዳው ሞተር ተጨዋች አማኑኤል በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች በደረጃ አራተኛው መባሉን ተከትሎ ኢትዮኪክ የተሰማውን እንዲገልፅልን ለጠየቅነው ሲመልስ

” በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ጌታ ለዚህ ታሪክ ስላበቃህኝ አመሠግነዋለሁ፤ እዚህ ትልቅ መድረክ ላይ በመመረጤ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት
የዋልያዎቹ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመሀል ሜዳው ሞተሩ አማኑኤል ዮሐንስ ደስታውን በአጭሩ ለኢትዮ ኪክ ገልጿል።