ዜናዎች

“ከቦትስዋና ጋር የተጫወትነው ጨዋታ 3 ለ 1 ብናሸንፍም በነበረን ቆይታ ጫናዎች ነበሩብን” – አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል

የኢትዮጵያውያ  ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ከቦትስዋና አቻው ጋር ከሜዳው ውጪ ያደረገውን ጨዋታ አስመልክቶ
አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል እና አምበሏ ናርዶስ ጌትነት በሸራተን አዲስ ከጋዜጠኞች በቀርቡ ጥያቄዎች እና የቡድኑን አቋም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ማክሰኞ ሰጥተዋል።

በቅድሚያ ግን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የቦትስዋ ጨዋታን አስመልክቶ የሚከተለውን ብለዋል

” የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከተዘጋጀንበት ጊዜ አኳያ እጅግ በጣም ደስ የሚል ዝግጅት ነበር። በቀን ሁለት ጊዜ የመስራትም አጋጣሚ ነበር። ከድካም ውስጥ ከጫና ውስጥ ስለመጣን ከነበረብን የስሴካፋ እና ድግግሞሽ ጨዋታዎች ስለነበረብን የትሬሊንግ ፕሮግራማችንን ቀይረን በቀን አንድ ጊዜ እንዲሰሩ አድርገናል። በተጨዋቾቼ ላይ እጅግ በጣም ደስ የሚል ተነሳሽነት ነበር ።ጥሩ ነገር ያሣዪ ነበር። ግን የአቅም ማነሶች ግን በአንዳንድ ተጨዋቾች ላይ ይታይ ነበር። ይኸም የጨዋታ መደራረብ ስለነበር ነው።ከዛ በተረፈ ዝግጁቱን በቀን አንድ ጊዜ በማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል”

በመቀጠል ስለ ቦትስዋና ጨዋታው አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ሲናገር ” ከሴካፋ ቆይታችን በኃላ ዝግጅት እና አንድ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገን ነው ከቦትስዋና ጋር የተጫወትነው ጨዋታውን 3 ለ 1 ብናሸንፍም በነበረን ቆይታ እናንተም እንዳያችሁት ጫናዎች ነበሩብን።የአየር ሁኔታው ሞቃት በመሆኑ ትንሽ አስቸግሮን ነበር። እንዲሁም የምሽት ጨዋታ በማድረጋችንም እንዲሁ ጫናዎች ነበሩ። እግር ኳስ ብዙ ጊዜ በስህተቶች የተሞላ ስለሆነ እኛም የሰራነው ስህተት ጫና ውስጥ ከቶናል። ስህተቶች 2 ለ 1 እየመራን እኛው በሰራነው ስህተት 1 ጎል ሲቆጠርብን ሌላ ጫና ተፈጥሮ ነበር ። ይህንንና የነበረቡንን ስህተቶች አስተካክለን ጨዋታው 3 ለ 1 አሸንፈናል” ብለዋል

ከአሰልጣኙ ንግግር በመቀጠል ጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለአሰልጣኝ ፍሬው እና የቡድኑ አምበል ናርዶስ ጌትነትን ጠይቀው  ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻ አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ከቦትስዋና አቻው ጋር በቀጣይ የመልስ ጨዋታቸውን አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚያደርጉ ገልፀው ቡድናቸው ዝግጅታቸውን መጀመራቸውን በአጠቃላይ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ድጋፍ ያደረጉትን አካላት ከልብ አመስግነዋል።