ዜናዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ጀምሯል !

ለኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ኢትዮጵያ ከጋና፣ ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ጋር በምድብ ሰባት መደልደሏ ይታወቃል።
ዋልያዎቹ በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ምድቡን በ9 ነጥብ  በሁለተኛነት  ከሚመራው የጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ደቡብ አፍሪካ ኦርላንዶ ስታዲየም ላይ ለሚድረገው ጨዋታ የመጀመሪያ ልምምዱን ዛሬ በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ሜዳ ላይ ጀምሯል። 
አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለዚህ ጨዋታ ለ26 ተጨዋቾች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በዛሬው የመጀመሪያ ቀን 22 ተጫዋቾችን ይዘው ጀምረዋል። ከ26ቱ ተጨዋቾች በዚህ ልምምድ ላይ በጉዳት ምክንያት ሱራፌል ዳኛቸው፣አማኑኤል ገብረ ሚካኤል ፣ ያሬድ ባየህ መገኘት አልቻሉም። ብሔራዊ ቡድኑ እስከ ቀጣይ ማክሰኞ ድረስ በቀን አንድ ጊዜ ልምምድ ማድረጉን የሚቀጥል ይሆናል።
Photo @Tikvah