ዜናዎች

የፈረሰኞቹ አዲሱ አሰልጣኝ ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች የታንዛኒያው ሲምባ ለማሰልጠን ሲቪያቸውን መላካቸው ተሰማ !

አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ   ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች ፈረሰኞቹን ከተረከቡ ከሁለት ወር ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላ ወላጄ አባቴ አርፏል በማለት ከቀናቶች በፊት ወደ ሀገራቸው መጓዛቸው ይታወቃል። ይሁንና የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች ሀዘን ብለው በተጓዙ በቀናት ልዩነት ከታንዛኒያው ሲምባ ጋር ከትላንት በሰቲያ ጀምሮ ስማቸው እየተነሳ ይገኛል።
የታንዛኒያው ፉትቦል ቲሺ ትላንት ባሰፈረው መረጃ የታንዛኒያው ሲምባ ክለብ ከአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ ጋር መለያየቱን ተከትሎ የሲምባ ክለብን ለማሰልጠን ፍላጎታቸውን አሳይተው ሲቪያቸውን የላኩትን አሰልጣኞችን ስም ይፋ አድርጓል።
እንደ መረጃው ከሆነ ከነዚህ አሰልጣኞች መካከል የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ሰርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲች ከነፎቶቸው  እንዲሁም ሆላንዳዊ ሃንስ ቫን ደር ፕሉዪጅም እና ሰርቢያዊ ኮስታዲን ፓፒች በዋነኝነት ለማሰልጠን ሲቪያቸውን የላኩ መሆናቸውን ጠቅሷል።
በተያያዘ መረጃ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አዲሱ አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፓቲች ወላጄ አባቴ አርፏል በማለት ወደ ሀገራቸው ቢያመሩም በአንፃሩ የተለያዪ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም የዛምብያውን ዜዝኮ ዩናይትድ ኣሰልጣኝ በነበሩት ጊዜ ክለቡን ሲለቁ በወቅቱ ያቀረቡት ምክንያት የአባታቸው ህልፈተ-ህይወት ሲሆን በወቅቱ ክለቡ በሰጣቸው ፍቃድ ወደ ሀገራቸው ቢጓዙም አሰልጣኝ ዝላትኮ ክሪምፖቲ ከክለቡ ሳይመለሱ መቅረታቸው ታውቋል።
እ.ኤ.አ በ2017 ወደ ሀገራቸው በአባታቸው ሞት ብለው ሲያቀኑ የቀድሞ ክለባቸው zesco በፌስቡክ ላይ  ይህንፅፎ ነበ
👇