ለኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በፈረንጆቹ October 5 ጋናን የሚያስተናግደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የባህርዳር ስታዲየም በመታገዱ ምክንያት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዚህ ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ለኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ መላኩ ታውቋል። በምድብ G በሶስት ነጥብ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በሁለተኝነት ከምትመራው ከጋና አቻቸው ጋር የሚያደረገው ጨዋታ ከሀገር ውጭ በናይሮቢ የሚገኘውን የኒያዮ ብሔራዊ ስታዲየም ለሚያደርግ ጎረቤት ኬንያን ጠይቋል ።
የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ውድድሮች በብቸኝነት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ አለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ካፍ በትናንትናው እለት ጥቅምት 7/2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል ። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አንድ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ባለመኖሩ በቀጣይ የሚኖሩ የብሔራዊ ቡድኑ እና ሌሎች አህጉራዊ ጨዋታዎች ተጨማሪ የጉዞ ወጪዎች እና የሆቴል ወጪዎችን እየሸፈነ ከሀገር ውጪ የሚካሄድ ይሆናል ።
– እገዳ የተጣበት የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም