አፍሪካ ዜናዎች

– ዓፄዎቹ አዲስ እና ነባር ተጨዋቾቹን በመያዝ ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ቀጥለዋል !

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው ፋሲል ከነማ ከሱዳኑ አሊሂላል ጋር ከጳግሜ 5 እስከ መስከረም 2/2014 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች በሜዳው ባህር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን እንደሚያደርግ የወጣው እጣ ድልድል ያመለክታል።
ለዚህ ዝግጅትም ዓፄዎቹ ከቀናት በፊት አዲስ ያስፈራማቸውን እና በ2013 ሻምፒዮና የነበሩትን ነባር ተጨዋቾቹን በመያዝ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ  ዝግጅታቸውን በባህር ዳር እያደረጉ እንደሚገኝ ታውቋል። በወጣው የካፍ የጨዋታ ፕሮግራም መሠረት ፋሲል ከነማ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን  በሳምንቱ ከመስከረም 7 እስከ 9/2014 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ወደ ሱዳን ተጉዞ የሚያደርግ ይሆናል።
ዓፄዎቹ አዲስ ያስፈራማቸው እና ነባር ተጨዋቾች በጥቂቱ