ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኦኪኪ አፎላቪ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን አኑሯል

የ2013 ዓ.ም ሻምፒዮና የነበረው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾች ውል ያደሰ ሲሆን ወሳኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
በዚህ መሠረት ከሀገሩ ናይጀሪያ ሆኖ የቅድመ ስምምነት የፈረመው ኦኪኪ አፎላቪ በዛሬው እለት ኢትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ለአንድ አመት የሚያቆየውን ውል ከዓፄዎቹ ጋር ፈርሟል ።