የ32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮሮና ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቶ ነገ በታዋቂው የጃፓን አርክቴክት ኬንጎ ኩማ በተሠራው ባለ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በፈጀው እና 68ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ያለ ተመልካች በሚደረግ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በይፋ ይጀመራል። በታሪካዊው እና ተጠባቂው የቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮዽያን ባንድራ በመከፈቻው ስነስርዓት ላይ ከፍ ለማድረግ ትላንት የተጓዘው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ከስድስት ሰአታት ቆይታ በኃላ ከኮሮና ነፃ መባሉ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት የመጀመሪያው ተጓዥ የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ በሀገራዊ ቀላማት ደምቆ ይታያል ተብሎ ይገመታል። በርግጥ ቡድኑ በቅርቡ ይፋ ያደረገው መለያ ትጥቅ ከዚህ ቀደሞቹ የኦሎምፒክ መለያ የትጥቆች ቀለማት አንፃር ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ላይ ከመወከል አንፃር ብዙም የሚጎላ አይደለም ማለት ይቻላል።
ነገ በይፋ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮዽያ ልዑካን አጠቃላይ ከ100 በላይ እንደተጓዘ ተዘግቧል ። ይህም በአትሌቲክስ ፌደረሽን በኩል 35 አትሌቾች 11 አሰልጣኞ ፣ 2 ሐኪሞች ፣ 3 ወጌሻዎች እና 4 ኦፊሻሎች በአጠቃላይ 55 የልዑካን ቡድን መጓዛቸው ተጠቁሟል። ከዚሁ በድን በቀጣዮቹ ቀናት የሚጓዙ አትሎች እንዳሉ ሆነው።
በሌሎች ስፓርቶች በውሀ ዋና ከአሰልጣኝ እና ከቡድን መሪ 3 ፣ ተኳንዶ በተመሳሳይ 3 ፣ ብሰኪሌት እንዲሁ 3 ሰፓርተኞች ብቻ ወደ ቶኪዮ መጓዛቸው ተገልጿል።
በተቃራኒው በኢትዮዽያ ልዑካን በኩል አጠቃላይ ከተጓዘው ከ100 በላይ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ብዙም ከስፓርት ጋር ግንኙነት የሌላቸው በልዑካን ቡድንነት መጓዛቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
እንደ መረጃውን ከሆነ በኮቪድ ምክንያት አትሌቶች ቢታመሙ በምትካቸው ተጠባባቂ አትሌቶች በመቀነሳቸው እና ያለመጓዛቸው ተጠቁሟል። ከላይ የተጠቀሱት ተጠባባቂ አትሌቶች ተቀንሰው ለምን የልዑካን ቡድኑ እንደበዛ ከውድድሩ በኋላ ማብራሪያ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ከዚሁ ጋር አምስት ጋዜጠኞች ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ተጠቁሟል። ምንጮች እንደጠቆሙን ወደ ቶኪዮ ለማቅናት የጋዜጠኞቹ ጉዞ በተመለከተ ውዝግብ መነሳቱ ተሰምቷል። አሁን ከተጓዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ በአትሌቲክ ብቻ ትኩረት አድረገው የሚዘግቡ በግላቸው ለመሄድ ጥረት ያደረጉ እንደነበር ቢሰማም ፣ጋዜጠኞቹ ወደ ስፍራው ሳይካተቱ ቀርተዋል።
ይህን እና ብዙ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን አምቆ ወደ ጃፓን የተጓዘው ልዑካን ቡድን በቀጣዮቹ ቀናቶች ትኩረት ከሚወስዱ ስፖርታዊ ክስተቶች አንዱ ይሆናል ።