ዜናዎች

– የሳምንቱ አንኳር የዝውውር መረጃዎች – ባህርዳር ከነማ አቡበከርን በከፍተኛ የወርሀዊ ደሞዝ አስፈረመ !

🔵ባህርዳር ከነማ
አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን ከቀናት በፊት የቀጠረው ባህርዳር ከነማ የተጨዋቾች የዝውውር ሂደቶችን በይፋ ማስፈረም ቀጥለዋል። ዛሬ በተሰማው መረጃ የጅማ አባጅፋሩን ወጣት ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በከፍተኛ ወርሀዊ ፊርማ የጣና ሞገዶችን መቀላቀሉ ታውቋል።
🔵ሐዋሳ ከተማ
በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን  የቀጠረው ሐዋሳ ከተማ የነባር ተጨዋቾችን ውል ማደስ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት የክለቡ ወሳኝ ተጨዋች የኤፍሬም አሻሞ እና ዳንሄል ደርቤ ዉል አድሷል።