ዜናዎች

ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሴካፋ ልምድ እንዲቀስሙ በባህርዳር ታደመዋል !

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በባህር ዳር ተገኝተው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድርን እንዲመለከቱ እና ልምድን እንዲቀስሙ እየተደረገ ይገኛል። ታዳጊዎቹ በቀጣይ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች መሆናቸውን እንዲያልሙ ለማድረግ  የታሰበ መሆኑን የፌዴሽኑ ዘገባ ያመለክታል።
ታዳጊ ቡድኑ በተጨማሪም በባህርዳር ልምምድም እያከናወኑ የሚገኙም ሲሆን በዛሬው ዕለት ባደረጉት ልምምድ የትናንቱን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታ መነሻ በማድረግ ዋና አሰልጣኙ እንድሪያስ ብርሀኑ እና ምክትል አሰልጣኝ አሳምነው ገብረወልድ ለተጫዋቾቹ ገለፃ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ከዚህ ቀደም ወደ እስራኤል ተጉዞ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ስብስቡ ሳይበተን በቀጣይ ለሚጠብቁት ውድድሮች ራሱን እያዘጋጀ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ዘገባ ያመለክታል።