ዜናዎች

የሴካፋ ተካፋይ ሀገሮች ዛሬ ባህር ዳር ገብተዋል !

በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት ዛሬ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በሚጀመረው የምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ከ23 አመት በታች ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ሀገራት አሁንም እየገቡ ይገኛል ።
በምድብ ሐ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን እና ተጋባዥ አገር የሆነው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዛሬ ማለዳ ገብተዋል።
ለውድድሩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሲዘጋጁ ቆየው የደቡብ ሱዳን እግር ኳስ ቡድን የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሃፊ ቪክቶር ሎውረንስ ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዙ በፊት እንዳሳሰቡት ” በሴካፋ ውድድር ሀገርን መወከል ብቻ ሳይሆን አሁች ዋንጫ ይዛችሁ የምትመጡበት ጊዜ።ነው ”እንዳሳሰቡት ” በሴካፋ ውድድር ሀገርን መወከል ብቻ ሳይሆን አሁን ዋንጫ ይዛችሁ የምትመጡበት ጊዜ ነው ” ብለዋል
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የገባው ተጋባዥ ሀገር የሆነው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቡድን ሲሆን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የገንዘብ ችግር አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ቡድኑ ኢትዮጵያ ደርሷል።የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት የሚገባ ይሆናል።
እንደሚታወሰው በሴካፋ ዛሬ ሲጀምር ዩጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ እንደሚጫወቱ ተጠቁሞ የነበረ ቢሆንም ኮንጎ በመዘግየቱ ምክንያት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።