ዜናዎች

– ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምበሉ ተለያየ!

በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ ላለፉት 12 ዓመታት በተከላካይ እና አማካኝ ስፍራ ያገለገለው አምበሉ ምንተስኖት አዳነ ከክለቡ መለያቱ ተረጋግጧል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ዘንድ “ፀባየ ሸጋ ” በሚል ስም የሚጠራው ምንተስኖት አዳነ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ከቡድኑ ተለያይቷል።
ምንተስኖት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ቆይታው ሰባት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ፣ሁለት የአሸናፊዎች አሸናፊ፣ስድስት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እና ሁለት የኢትዮጵያ ዋንጫ ድሎች ላይ ሚናውን ተጫውቷል። ተጨዋቹ ከታዳጊነቱ ጀምሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት በድምሩ 16 ዋንጫዎችን ከፍ በማድረግ የስኬት ዓመታትን አሳልፏል።  የቅዱስ ጊዮርጊስ 23 ቁጥር መለያ ለባሹ አምበሉ  ምንተስኖት አዳነ ፈረሰኞቹን ተሰናብቷል ።