ዜናዎች

ሲዳማ ቡና አራተኛውን ተጫዋች ከሃዲያ ሆሳዕና አስፈርሟል !

ተስፋዬ በቀለ
በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ተስፋዬ በቀለን ከሃዲያ ሆሳዕና አስፈርሟል።ተጫዋቹ በተለምዶ  የአማካይ ተከላካይ  ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሚጫወት ሲሆን የክለቡን የጀርባ ተከላካዮችን ክፍተት ለመሙላት ሁነኛ ፈራሚ በመሆን ክለቡን በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በመቀለ 70 እንደርታ ካሰለጠኑት ከቀድሞው አሰልጣኝ ገ/መድህ ሀይሌ ጋር በሲዳማ ቡና የሚገናኝ ይሆናል።
ሲዳማ ቡና ከዚህ በተጨማሪ ሁለት የመስመር አጥቂዎችን ከኮልፌ ቀራኒዮ  በከፍተኛ ሊግ  ብሩክ ሙሉጌታ እና አንዋር ዱላ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ለሲዳማ ቡና ለመጫወት በመስማማት ፊርማቸውን አኑረዋል።  የኢትዮጵያ ቡናው  ግብ ጠባቂነት  ተክለማርያም ሻንቆ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት የሁለት ዓመት ውል ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል ። 
ከሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ