ዜናዎች

– ለሴካፋ ሻምፒዮና የባህር ዳር ስታዲየም 25 ሺህ ተመልካች ተፈቀደ ! አባል አገራት ከሐምሌ 7 ጀምሮ ይገባሉ

ከግራ ወደ ቀኝ አቶ አበበ ገላጋይ.እና አቶ ሰሎሞን ገ/ሥላሴ

 

በባህር ዳር ከተማ ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ውድድር በፌዴሬሽኑ የተቋቋመው የሴካፋ ብሔራዊ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ዛሬ ሐምሌ 1/11/2013 ዓ.ም  ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለሚዲያ አካላት መግለጫ  ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ.እና የፌዴሬሽኑ ም/ ዋና ፀሐፊ እና የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ሰሎሞን ገ/ሥላሴ መግለጫውን ሰጥተዋል።
በመግለጫው ውድድሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአማራ ክልል ጋር በመቀናጀት በማዘጋጀቱ የአገሪቷ ወጣቶች በእግር ኳስ ተሳትፎ በማግፕታቸው በእግር ኳሱ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የአገራችንን ገጽታ ለመገንባት ትልቅ እድል ይፈጥራል።ለእዚህም የውድድር ኮሚቴው በቅድመ ውድድር ፕሮግራሙ ኮሚቴዎችን ከባህር ዳርና ከፌዴሬሽኑ በተውጣጡ አባላት በማዋቀር ወደ ስራ በመግባት ለውድድር አስፈላጊ የሆኑ የውድድርና የልምምድ ሜዳዎች፣ የኮቪድ 19 እና ዶፒንግ፣ የፀጥታ፣ መስተንግዶ እና አቀባበል እንዲሁም መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ እየተሰራ እንደሆነ  ተጠቅሷል።
ውድድሩ ከሐምሌ 10 እስከ 25/2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ እና ተሳታፊ የሆኑት 11 የሴካፋ አባል አገራት ከሐምሌ 7 ቀን 2013 ጀምሮ ወደ ባህርዳር እንደሚገቡ እና የኮሚቴው አባላትም በተቀናጀ መልኩ በባህር ዳር ውድድሩን በድምቀት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ታውቋል ።
በመጨረሻም በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት የባህር ዳር ስታዲየም ከሚይዘው የተመልካች ብዛት አንድ አራተኛ (ሃያ አምስት ሺህ ) ተመልካች እንደተፈቀደና በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት እንደሚስተናገድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ ገልፀው ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
@የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን