ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የመጨረሻውን ዕድል ተጠቅመን ወልቂጤ ከተማን በሊጉ ለማቆየት የተቻለንን ሁሉ መሠዋት እናደርጋለን”- አቡበከር ሳኒ

አቡበከር ሳኒ ከቡደን አጋሪችሁ ጋር

 

የወልቂጤ ከነማ በዘንድሮው ቤትኪንግ ጅማሮ ላይ የተሻለ የእግር ኳስ እና በጥሩ ውጤት ዓመቱ ያጠናቅቃል ተብሎ የተገመተ ቡድን ነበር። በአንፃሩ የኮቫድ ወረርሽኝ ምክንያት ቡድኑ በውስጡ ይዟቸውን የነበሩትን ድንቅ ብቃት የነበራቸው ተጨዋቾች እስከመጨረሻው ማሳየት ሳይችል ክለቡ ከወራጅ ቡድን አንዱም ሆኖል።
በቡድኑ የግል ብቃታቸው የተሸሉ እንቅስቃሴ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ደግሞ አቡበከር ሳኒ ነው።እንደሚታወቀው  በ2013 የኢትዮጵያ የቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ወራጅ የነበሩ  ሶስት ክለቦች  በሶስቱ የትግሪይ ቡድኖች ምትክ  ለመግባት በከፍተኛ ሊጉ ከየምድቡ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ካጠናቀቁ ክለቦች ጋር የፊታችን ሰኔ 18 ለሚያደርጉት ታላቅ ውድርር የአቡበከር ወልቂጤ ከተማ በሐዋሳ ይገኛሉ። ወልቂጤ ከተማ  ዳግም ወደ ቤትኪንግ ለመግባት  የሚያደርገውን ፍልሚያ በተመለከተ ከኢትዮኪክ  ጋር አቡበከር ሳኒ ቆይታ  አድርጋጓል ።
ኢትዮ ኪክ :- ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ በሚደረገው ጨዋታ ሐዋሳ ዝግጅት ላይ ናችሁ ?
አቡበከር :- አዎ ዝግጅት ላይ ነን…
ኢትዮ ኪክ :-  ዝግጅቱ  በሐዋሳ እንዴት  ነው  ?
አቡበከር :- አሪፍ ቆይታ ላይ ነን፣ በቀን አንድ ጊዜ  ልምምድ እየሰራን ነው።
ኢትዮ ኪክ :- ዘንድሮ ቤትኪንግ ጅማሪያቹ አሪፍ ሆኖ መቀጠል ያልቻላችሁት በአንተ እይታ  ምንደን ነው ?
አቡበከር :- በጣም ከባድ ጥያቄ ነው። ለራሴም እስካሁን ምላሽ አላገኘሁለትም……..
ኢትዮ ኪክ :- አብዛኞቻቹ ተጨዋቾች ጥሩ ስብስብ ነበራችሁ ምን ሊሆን ይችላል?
አቡበከር :- ምናልባት ትኩረት ማጣታችን ይሆናል ለተደጋጋሚ ሽንፈት የዳረገን ።
ኢትዮ ኪክ :- ምናልባት አሰልጣኛቹ ከተወሰነ ጨዋታ በኃላ መታመማቸውሰ ?
አቡበከር :- እሱ በአንድ በኩል ጉዳት አለው። አሰልጣኝ ከጎን ሲኖር በጣም የተሻለ ነገር ነው።
ኢትዮ ኪክ :- በዘንድሮው ዓመት ብቻ ሶስት አሰልጣኝ ተለዋውጠዋል ተጨዋች ሆኖ የአሰልጣኝ ቶሎ መለዋወጥ የሚኖረው ስሜት ይኖረው ይሆን ?
አቡበከር :- ያው ከባድ ነው። ግን ያን ያክል የፈጠረው ችግር የለም …….
ኢትዮ ኪክ :- ስለዚህ  አሁን ከአዲሱ አሰልጣኝ ጋር በመተባበር ይሳካልናል ትላልህ  ?
አቡበከር :- አዎ በጣም እናሳካዋለን ። የምናገኘውን የመጨረሻውን ዕድል ተጠቅመን ወልቂጤ ከተማን በሊጉ ለማቆየት የተቻለንን ሁሉ መሠዋት እናደርጋለን።
ኢትዮ ኪክ :- የዘንድሮ  በ2013 የኢትዮጵያ የቤት ኪንግ ፕሪሚየር የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች በአንተ እይታ ማን ነው ?
አቡበከር :- ያው ግልጽ ነው አቡበከር ናስር ይገባዋል….
ኢትዮ ኪክ :-ከወልቂጤ ጋር ኮንትራትህ መቼ ያልቃል?
አቡበከር :- አንድ አመት ይቀረኛል።
ኢትዮ ኪክ :- ስለዚህ ከቡድኑ ጋር ትዘልቃለህ ?
አቡበከር :- እስከአሁን ባለው ሁናቶ አዎ ።
ኢትዮ ኪክ :- አመሰግናለሁ
አቡበከር :- እኔም  አመሰግናለሁ