ዜናዎች

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የቫር ዳኝነቱን ይመሩታል !

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ (ቫር)

 

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሞሮኮው ግዙፍ ቡድን ዊድዳድ ካዛብላንካ እና በደቡብ አፍሪካው ካይዘር ቺፍ መካከል የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ነገ ሰኔ 12 እና በቀጣይ ሳምንት ሰኔ 19 ያደርጋሉ።ሁለቱ ቡድኖች በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የነገውን የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ጨዋታቸውን በሞሮኮ ስታዲየም የሚካሄዱ ሲሆን ሴኔጋላዊው ማጉቴ ንዲያዬ በመሀል ዳኝነት እና ከጋምቢያው ባካሪ ፓፓ ጋሳማ ደግሞ በቫር ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ሁለቱ ቡድኖች በሳምንት ልዩነት ደቡብ አፍሪካ ላይ በሚያደርጉት የሁለተኛ ዙር ወሳኝ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቫር ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።
እንደሚታወሰው የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ከሳምንታት በፊት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ ቅሬታውን ማቅረቡ ታወሳል።
የሞሮኮው ዊይዳድ ካዛብላንካ የቅሬታው ምክንያት  ደግሞ አልጀርስ ላይ ከአልጄሪያው ሚሲ አልጀርስ   ጋር 1 ለ1 አቻ ውጤት በተጠናቀቁት ጨዋታ ላይ በመሀል ዳኝነት የመሩትን ኢትዮዽያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቻቸው ላይ ዳኝነት ቅሬታን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በማስገባት ዳኞቹን ክፉኛ ተቃውሟል ፡፡
ይሁንና ካፍ የሞሮኮው  ዋይዳድ  ካዛብላንካ  ተቃሞውን በመተው ኢትዮጵያዊውን ኢንተርናሽናል  ባምላክ ተሰማን  ቅሬታ አቅራቢው በሚያደርገው በጨዋታ ላይ በቫር ዳኝነት የሚመሩት  እንዲመሩ መርጧል።