የስዊዘርላድ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አባል የሆነውና የወደፊት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ በውሰት ሰጥቶት የነበረው የቀድሞ ክለቡ የስዊዘርላዱ ኒው ሻቴል ሙሉ ለሙሉ የራሱ በማድረግ የሁለት ዓመት ውል በዛሬው ዕለት አስፈርሞታል።
ከኢትዮጵያዊያን ወላጆቹ ስዊዘርላንድ ውስጥ ተዎልዶ ያደገው ተስፈኛው ወጣት ማረን ሀይለስላሴ ከአደገበት ኤፍ ሴ ዙሪክ በተውሶ በ2019 ዓ.ም. ለግማሽ ዓመት በራፐርስቪል በኃላም ፣ በ2019/2020 ደግሞ በውሰት ለኒውሻቴል ክሳማክስ መጫወቱ ይታወሳል።
ባለፈው የውድድር ዘመን ደግሞ በተውሶ ለኤፍ ሲ ቪል ውስጥ ቡድኑ ካደረጋቸው 36 ጨዋታዎች መካከል በ35 ተሰልፎ በመጫወት 7 ጎሎች አስቆጥሮ 3 ለውጤት የበቁ ጎሎችን አመቻችቶ በማቀበል ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል።
ፍጥነቱና የተለየ የኳስ ጥበቡ ያለው ማረን ኤፍሴ ዙሪክ ልምድ እስኪቀስም ድረስ በተውሶ እንጂ አሳልፌ አልሸጥም ሲል ቢቆይም በቀጣይ የ ውድድር አመት ያካበተው ልምድ ከበ ቂ በላይ ነው በማለት የቀድሞ ክለቡ ለኒው ሻቴል ክሳማክስ ሙሉ ለሙሉ የግሉ በማደረግ የሁለት ዓመት ውል አስፈርሞታል። ለዝውውር የተከፈለውን ገንዘብ ሁለቱም ክለቦች ለመግለጽ ፈቃደኛ ሳይሆኑም ቀርተዋል።ማረንን ዛሬ ያስፈረመው ኒው ሻቴል ክሳማክስ በድረ ገፃቸው ” ማረንን የእኛ አድርገን ማስፈረም በመቻላችን ደስታችን ወደር የለውም የሚል መልዕክት ” አስተላልፈዋል።