ዜናዎች

በኢትዮጵያ ቡናው ኮከብ አቡበከር ናስር የውጭ ክለቦች ትኩረታቸውን ቀጥለዋል !- የጆርጂያው ክለብ ቡናን እየጠበቀ ይገኛል !

አቡበከር ናስር
የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ እና የዘንድሮውን የቤትኪንግ  የጎል አግቢነቱን ሪከርድ በ29 ጎሎች በመስበር የውድድር ዓመቱን በሶስት የኮከብነት ሽልማቶች ያጠናቀቀው አቡበከር ናስር ላይ የተለያዩ የውጭ ሀገር ክለቦች ትኩረታቸውን መጣል ቀጥለዋል።
በዘንድሮው የ DSTV የቀጥታ ሽፋን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፉ ደረጃ መታየት በቻለው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ላይ  አቡበከር ናስር ድንቅ ብቃት ማሳየቱ ከኢትዮጵያ አልፎም በሌሎች ሊጎች ተፈላጊነቱን  የበለጠ ጨምሮም  እየታየ ይገኛል።
ከቀናት በፊት የጆርጂያው ” FC Dila Gori’ ክለብ አቡበከርን ለማስፈረም ለኢትዮጵያ ቡና በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል ።  በFC Dila Gori ክለብ በኩል ከኢትዮጵያ ቡና ክለብ ምላሹን  እየተጠበቁ እንደሆነ  ቢታውቅም ፣  ባአንፃሩ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሙሉ ለሙሉ ዝምታን መርጧል።
በተያያዘ የሰሜን አፍሪካ ክለቦች ግዙፍ ኤቶይል ስፖርቲቭ እና የደቡብ አፍሪካ ክለቦች ለክለቡ ጥያቄ ማቅረባቸው የቀጠሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ስፓርት ክለብ ሌሎች ዕድሎችን እየጠበቁ እንደሆነ  መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
በአንፃሩ የኢትዮጵያ ቡናው የዘንድሮው የጎል ኮከብ አቡበከር ናስር በዘንድሮ የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ያሳየውን ብቃት በጆርጂያ ሊግ በአንድ የውድድር ዓመት 20 ጎሎች ማስቆጠር ቢችል ሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ዕድሎች ሊከፈትል እንደሚችል የስፓርት ባለሙያዎች ለኢትዮ ኪክ ተናግረዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ከጆርጂያ የመጣውን ዕድል የማይቀበለው እንደሆነ ተሰምቷል ።