ዜናዎች

የመኪና አዳጋ ያጋጠመው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ፓትርክ ማታሲ ወቅታዊ መረጃ

ፓትርክ ማታሲ ክኤድዊን ፍሪምፖንግ ጋር
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትርክ ማታሲ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ መጠናቀቁን ተከትሎ ያሳለፍነው ቅዳሜ ረፋድ ላይ ከ አዲስ አበባ ወደ ኬንያ ወደ ቤተሰቡ ያቀናው። በአንፃሩ ትላንት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ኬኒያዊው ፓትሪክ ማታሲ በምዕራባዊው ኬኒያ ከካፕሳቤት  ወደ ካካአመንጋ  ከተማ ከቤተሰቡ ጋር በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳለ የመኪና መገልበጥ አደጋ አጋጥሞት በፍጥነት ወደ አቅራቢያ ሆስፒታል መወሰዱ መዘገቡ ይታወሳል።
አደጋው በደረሰበት ጊዜ ፓትሪክ ማታሲ ከሚስቱ ፣ ከሁለቱ ልጆቹ እንዲሁም ከአማቾቹ ጋር የቀድሞው  እግር ኳስ ክለቡ ከሜዳው ውጪ ያሸነፈበትን ጨዋታ መታደማቸው ነበር ።በኃላም እኩለ ቀን አካባቢ ማታሲ መኪናውን እያሸከረከረ እንደነበረ ሲገለፅ ከመኪናው ጎማ ጋር በተያያዘ ችግሩን መቆጣጠር አቅቶት አደጋው በከፋ ሊከሰት እንደተቻለ ተጠቁሟል።
በአሁን ሰዓት ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፓትርክ ማታሲ  በአካሉ ላይ በትከሻው እና በጭንቅላቱ ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱም ተዘግቧል። በአደጋው ​​ከነበሩ አምስት ሰዎች መካከል የሶስት ዓመት ወንድ ልጃቸው የከፋ ጉዳት የደረሰበት መሆኑ ሲገለፅ በከፍተኛ በጉዳቱ የግብ ጠባቂው ሚስት እግሯ ላይ እና ሌላኛዋ ህፃን  ልጁ ላይ ጉዳት እነደደረሰባት ተጠቁሟል። ምናልባትም ዛሬ የቀዶ ጥገና የህክምና እርዳታ ሊደረግላቸው እንደሚችል ዘገባዎች ያመለክታሉ።