ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“በእግርኳስ ሆኜ ማድረግ  የማሰበው ለእናትና አባቴ የተመቻቸ የሚኖሩበትን ቤት ነው፣ ኢንሽ አላህ ይሳካል ብዬ አስባለሁ “አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)

አቡበከር ናስር – ኢትዮጵያ ቡና

የ2013 የቤትኪንግ ኢትዮዽያን በ29ጎሎች በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ያጠናቀቀው በአቡበከር ናስር የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ  አድርጓል።

ወላጆቹ ዛሬ በስታዲየም እንደሚታደሙ ቀድሞ ያውቅ ነበረ?
” ምንም የማውቀው ነገር የለም ማን እንዳመጣቸው፣   ይመስለኛል የሱፍ መሠለኝ።በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ያላሰብኩት ነገር ቤተሰቦቼ መጥተው ማየታቸው አንደኛ በጣም ደስ ብሎኛል”
በእግርኳስ ተጨዋችነት ሆኖ ማድረግ አለብኝ ከሚለው ነገር ?
“በእግር ኳስ ውስጥ ሆኜ ድረግ  የማሰበው ለእናትና አባቴ በቃ እየተመቻቸ የሚኖሩበትን ቤት ነው የማስበው ፤ ኢንሽ አላህ ፤ ከአላህ ጋር ይሳካል ብዬ አስባለሁ “
የዘንድሮው ኮከብ ተጨዋች በአቡበከር ዕይታ  ማን ነው ?
” በፈገግታ…. “
ካንተ ውጭ
” እንደዛ እኔንጃ (በፈገግታ)”
ደጋፊዎች ዛሬ ሜዳ ውስጥ መግባታቸው የተለየ ስሜት ነበረው?
” በሚገባ ! ምክያቱም እኔ ከዚህ የበለጠ የሚመጡ ነበረ የመሰለኝ ። ግን በጣም ደስ የሚል ነገር ነው። ምክያቱም አመቱን ሙሉ ሳናያቸው ነበረ ። በዚህ አጋጣሚ ማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ላልመጡትም እንኳን ደስ ያላችሁ እላለሁ’