በ2013 የውድድር ዓመት የኮከብ ግብ አግቢነት ሪከርድ የሰበረው አቡበከር ናስር በዛሬው ጨዋታ ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ የጎል ሪከርዱን 29 አድርሷል።ከጨዋታው በኋላ አቡበከር ናስር ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ከጨዋታው በፊት የቡድን ጓደኞቹ “27 ” ለብሰው በተለየ ክብር መግባቱ የተለየ ሞራል ስለመስጠቱ ?
” እኔ ምንም እንደዚህ አልጠበኩም ነበር። እኔንጃ …ግነ በጣም ደስ ብሎኛል። መልበሻ ቤት ወስጥ ነው መኖሩን ያወኩት። እኔ በጣም ደስ ብሎኛል። ተጨዋቾቹን ጓደኞቼን በጣም አመሠግናለሁ”
በጨዋታው ሁለት ጎሎች ማስቆጠሩ እና ጨዋታው ከብዶት እንደነበረ ?
” አዎ ዛሬ ጨዋታው ከብዶኝ ነበር። ምክንያቱም ትንሽ አሞኝ ነበረ። እና ሜዳው እራሱ በጣም ደረቅ ነው። የሚመለከተው አካል ሊያስብበት ይገባል። ሜዳው በጣም ከባድ ነው። ለእኛም ከባድ ስለነበረ፣ጫና ውስጥም ስለነበርን እና ውጤቱ የግድ ያስፈልገን ስለነበረ አላህ ብሎ አሳክተንዋል”
ዛሬ ያስቆጠረውን 29 ጎሉን የሰጠው ታፈሰ ነው፣ ከዚህ ቀደም 29 ጎል ታገባለህ ያለው ተገጣጥሞብኸል?
” ( በፈገግታ) አዎ እኔ በቃ ጭንቀት ውስጥ ስለነበርኩ አሁን አስታወስከኝ፤ ግን ብሎኝ ነበር 29 ጎል ታገባለሄ ብሎ ፤ ገና ዝግጅት ላይ ነበረ ሲለኝ የነበረውና ታፈሰንም በዚህ አጋጣሚ ማመስገን እፈልጋለሁ“
አንድ ጨዋታ ከአዳማ ጋር አላቸው በእሱ ግምት ምን ያህል ጎል ላይ ያቆማል ?
” ያው ኢንሸ አላህ ፣ ከአላህ ጋር ብዙ ሰዎች 30 እያሉኝ ነበረ….ያው አሰልጣኞችም ብዙ በቃ የስፓርት ስዎች 30 ብለው ነበር ። ኢንሸ አላህ ቀጣይ ጨዋታ ወይ ከዚህ ይበልጣል …ያው አላህ ነው የሚያውቀው እንግዲህ”
በግል ጥረትህ ወይስ በኢትዮጵያ ቡና እንቅስቃሴ ነው ብዙ ጎሎች ያስቆጠርከው ?
” አይ ይሄማ በእንቅስቃሴው እና በጓደኞቼ ጥረት ነው እንጂ ፤ ያው ብቻዬን ምንም የምፈጥረው ነገር የለም። ያው ጎደኞቼ በሚያደርጉት ጥረትና በሚሰጡኝ ኳስ ነው እንደዚህ ያገባሁት እና በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ፣ ሙሉ የአሰልጣኞች ሁሉንም ስፓርተኛም ተጨዋቾችን በጠቅላይ ለቡና ቅርብ ያሉትን ማመስገን እፈልጋለሁ”
ለአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ለመሳተፍ ጫፍ ላይ ከመደርሳቸው አኳያ ለማለፍ ያንን ታሳቢ ስለማድረጉ
“አዎ እኛ በቃ በመጀመሪያ ስንነሳ ለዋንጫ ነበረ፣ ሲቀጥል ግን ሁለተኛ ሆነን ነው ልንጨርስ ያሰብነውና ። አሁን በቀጣይ ጨዋታ ነው ፣ እኛ አቻ ይበቃናል ግን ቀጣይም ለማሸነፍ ነው የምንገባው ፣ አዳማም አሪፍ ቡድን ነው። ቀጣይ የተሻለ ነገር ለማምጣት እንጥራለን”