በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሊጉ የተቀላቀለውና በዘንድሮው የቤትኪንግ ጅማሮ ላይ ጠንካራ ቡድን የነበረው ወልቂጤ ከተማ በዛሬው ጨዋታ ከሐዋሳ ከተማ ጋር ያለ ጎል መለያየቱ ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ላይ በጭንቀት እንዲጠብቅ ያደረገዋል። የዛሬው ጨዋታ እንደተጠናቀቀ በወልቂጤ ከተማ በኩል ተጨዋቾቹ እያዘኑ ከሜዳ ሲወጡ ታይተዋል።በተለይም የወልቂጤ ከተማው ግብ ጠባቂ እና የቡድኑ አምበል ጀማል ጣሰው የዛሬው ጨዋታ ሲጠናቀቅ ከሜዳው እያለቀሰ ነበር የወጣው።
ከጨዋታው በኋላ ጀማል ጣሰው ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ጨዋታው ነጥብ ያጡበት እና የሚያስቆጭ ጨዋታ መሆኑን በተመለከተ ?
” አዎ ፣ ማለት ውጤት ከመፈለጋችን አንፃር በጣም የሚያስቆጭ ጨዋታ ነው። ማረግ እየቻለን እየቻልን ያላረግናቸው ጨዋታዎች ስለነበሩ ለዛ ነው በጣም የተቆጨውት በጣም “
ከሜዳ ሲወጣ እያለቀሰ ስለመሆኑ
” አዎ ማለት እየረፈደብን ስለሆነ ሁለት ጨዋታ ነው ቀሪ ያለን ይሄን ጨዋታ ግዴታ ማሸነፍ ነበረብን እና እሱ ነው ያስቆጨኝ”
ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች በሲዳማ እና ድሬዳዋ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ
“በራሳችን ኦጅ ነው ያለው። የሌላ ቡድን ጨዋታ ለእኛ አይገባንም። እኛ ራሳችን ነው ማሸነፍ ያለብን። ስለዚህ የምንገጥማቸው ቡድኖች ደግሞ ከባድ ናቸው ። ዕድላችን ይሄ ነበረ ብዬ ነበር የማስበው ለዛ ነው በጣም ያዘንኩትይ “
የዓመቱ ጥረታቸው እና ያገኙት ውጤት ተገቢ ስለመሆኑ
” አይገባንም ። ማለተ ስንጀምር ጦሩ ነበረን በኃላ ላይ ከነበረን ነገር እየወጣን ፣ መጀመሪያ ላይ ኳስ ነበር የምንጫወተው ከዛ ነገር እየወጣን ስንመጣ የማንፈልገውን አጥተነዋል። በራሳቾን እጅ ነው ያጣነው።አይገባንሞ”
ትላንት በብሔራዊ ቡድን ስለተሸለሙት ልየዮ ሽልማት ማግኘታቸውን በተመለከተ የተሰማው
” በትላንቱ ሽልማት በጣም ነው ደስ ያለኝ ፣ አሁን ግን ጥሩ ስሜት ላይ አይደሉም። ትላንት ደስተኛ ነበርኩኝ ። ይሄ ነገር መቀጠል አለበት። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብዙ አመት ነው ያገለገልነው እና ለዛ እውቅና ስለተሰጠኝ በጣም ደስ ብሎኛል። ይሄ ነገር መቀጠል አለበት ነው የምለው ።
ቻል ዘንድሮ አለ ዘፈን!