በ23ኛው የዛሬ ሁለተኛ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና እና የሰበታ ከተማ ከፍተኛ የመሸናነፍ ትግል የታየበትና በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ነው። በተለይም በሀዲያ ሆሳዕና እና የሰበታ ከተማ ጨዋታ 2 ለ 2 በአቻ ውጤት እንዳይቋጭ ለሰበታ ከተማ ወሳኝ የሆነውን የማሸነፊያውን ግል ዱሬሴ ሹቢሳ በ95ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። ተጨዋቹ ለቡድኑ በባከነ ሰዓት አስቆጥሮ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ እንዲገኝ አስችሏል። ዱሬሴ በዚህ መልኩ ጎል ሲያስቆጥር የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከጨዋታው በኋላ ዱሬሴ ሹቢሳ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
በመጨረሳ ሰአት ለቡድኑ ስላስቆጠረው የማሸነፊያ ጎል በተመለከተ
” ጎሉ በጣም ያስፈልገን ነበር። በጣም አስፈላጊ ነጥብ ነበረ። የመጣንበት ነገር በውጥረት ውስጥ ነበረ። በስነልቦና ካለፈው ጨዋታ አንፃር ይሄ የምንፈልገው ውጤት ነበረ እሱን በኔ በኩል በማሳካቱ በጣም ደስታ ተሰምቷል”
ከዚህ በፊት ተቀይሮ ሲገባ ጎሎች አስቆጥራለሁ ብሎ ነበር ፣ ዛሬስ።ይህን ማለቱ ?
” ዛሬ የኳስ ሂደቱ ነው እንግዲህ። ያው ከዚህ በፊተም ጎል ሳገባ የሰጠኝ የፊት አጥቂው(ማዎሊ) ነው። ልምምድ ላይ በምናደርገው ነገር ነው ።ያው ማንም አጥቂ ሲገባ ጎል ለማግባት ነው የሚገባውና ቲሙን ለመቀየር እኔም ያንን አስቤ ነው የገባሁት። ከእግዚአብሔርም ጋር ተሳክቶልኛል።
ደስታህን በልዪ ሁኔታ ወደ አሰልጣኝ አብራሃም መብራቱ ጋር ሄዶ የገለፀበት ምክንያት
” ጎሉን አስቆጥሬጰአሰልጣኛችን ጋር የሄድኩበት ምክንያት አንደኛ የቡድን መንፈሳችን ጥሩ አልነበረም። ጥሩ ያልነበረበት ምክንያት ደግሞ ከክፍያ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቡድኑ በስነልቦና ጥሩ ስላልነበረን ከውጤቱ እና ከደስታው አንፃር ደስታዬን መቆጣጠር ስላቃተኝ ነው፣ ወደ አሰልጣኛችን የሄድኩት”
እግር ኳሱ በዲ ኤስ ቲቪ በመታየቱ ታውቂያለሁ ብለህ ታስባለህ ለሚለው ?
” በጣም ታውቂያለሁ ። ከዚህ የበለጠ ደግሞ መስራት እንደምችል አምናለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር የተሻለ ነገር አደርጋለሁ”