የ23ኛው ሳምንት የመጀመሪያው ቀን ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና ጅማ አባ ጅፋር በ 1ለ1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው ላይ ከታዩ የሁለቱ ቡድኖች የመሸናነፍ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ በጅማ አባጅፋር በኩል ወጣቱ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በጨዋታው ብዙ ኳሶችን ከማምከኑ ውጭ በጥሩ አቋም ላይ መሆኑን አሁንም አሳይቷል። ከጨዋታው በኃላ አቡበከር ከሱፐር ስፓርት ጋዜጠኛ ሰኢድ ኪያር ጋር ቆይታ አድርጓል ።
የውድድር ዓመቱ ሲጀምር በቀይካርድ ከወጣ በኋላ አሁን ላይ ጥሩ መሆኑን በተመለከተ
” ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከባድ ነበር። አሁን ዕድሉ ተሰጥቶኝ በዕድሌ እየተጠቀምኩ ነው የምገኘው። ያው ሶስቱንም ጨዋታ በጥሩ መንፈስ እጨርሳለሁ ብዬ አስባለሁ”
አብዛኛውን ጊዜ አሰልጣኞች ከውጭ በመጡ በረኞች ላይ እምነት ያሳድራሉ እና በዚህ ላይ ያለው አስተያየት?
” አዎ ልክ ነው። ለውጭ ግብጠባቂዎች እነሱ በጣም ዕድል ይሰጣል። ምክንያቱም እኛ አያምኑብንም በብዛት ። ምንም አይከብድም ይኸው እየታየ ነው። ግን ቢያምኑብን ብዙ ወጣቶች አሉ እንደኔ መጫወት የሚችሉ አቅም ያላቸው። ሱፐር ሊግም አሉ እና እና አሰልጣኞቹም ቢያስቡበት እላለሁ።
የመጀመሪያ የውድድር ዘመንህ ነው፣ ዕድሜ ስንት ነው?
” ዕድሜዬ 22″
ብሔራዊ ቡድን ወደፊት የመሠለፍ ፍላጎቱ ?
“አዎ ቀጣይ ዓመት ተጠናክሬ አሪፍ ሆኜ ለመቅረብ እሞክራለሁ። ክረምቱንም በደንብ ተዘጋጅቼ እመጣለሁ። ሰውነቴ ላይ ያሉብኝን ክፍተቶች በሙሉ ሰርቼ ቀጣይ ዓመት እመጣለሁ።
ጅማአባጅፋር ካልወረደ ቢሆንም ቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች በተመለከተ ?
” ቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች የተሻለንን እናደርጋለን። አሁን ቡድናችን ከበፊቱ እየተሻሻለ ነው። እኛም እየሰራን ነው። ግን ጨዋታው አነሰች ግን እናያለን።
አቡበክር ኑራ ኢሉ አባ ቦር ዞን ከአልጌ ሳቺ ወረዳ ከሱጴ 01 ቀበሌ የወጣ ታታሪ የግብ ጠባቂ ነው። ትምህርቱን ሠስዋት አድርጎ ነው ከልጅነቱ ጀምሮ ወደ ግብ ጠባቂነት ያተኮረው። ልጁ በሱጴ ቀበሌ ውስጥ መሌኮ በሚባል ሜዳ ላይ ህጻናትን ሰብስቦ ጎል እንዲያስቆጥሩበት በማድረግ ብቻውን እየተለማመደ ያደገ ልጅ ነው። ከመሌኮ ሜዳ እሱን ማጣት አይታሰብም። በትንሽም በትልቁም ጨዋታ ውስጥ ግብ መጠበቅ ነው ፍላጎቱ።
አቡበክርን በዚህ ደረጃ በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ። በነገራችን ላይ ሱጴ 01 ቀበሌ ማለት ተዋቂው ደረሲ በአሉ ግርማ የተወለደባት መንደር ናት። ከዞኑ ዋና ከተማ መቱ 42 ኪሜ ወደ ምስራቅ ገባ ብላ የምትገኝ አነስተኛ ቀበሌ ናት።
I want to see him in a national team squad. He is talented and full of energy. Gobez!