ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ዋንጫው ለእኛ የተለየ ስሜት ያለው ፤ የዛሬውን ጎሉን አቀባዩ እኔ ሆኜ ሙጂብ ቢያገባ ደስ ይለኝ ነበር”- ሽመክት ጉግሳ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሻምፒዮናው ፋሲል ከነማ ዛሬ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ድሉን የበለጠ አጣጥሟል። በረፋዱ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ ጎሏን አማካዮ ሽመክት ጉግሳ አስቆጥሮ ወልቂጤን 1 ለ 0 መሻነፍ ችለዋል።ከጨዋታው በኋላ ሽመክት ጉግሳ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ዋንጫ ማግኘቱ እንዴት ይገለፃል?
” ዋንጫው ለእኛ የተለየ ስሜት ነው ያለው። የይህን ሶስት አመት በጣም ለፍተናል ። ብዙ ጥረናል። ግን እግዚአብሔር አላሳካውም።አሁን ግን ከሶስት ዓመት በኃላ ስላሳካልን እጥፍ ድርብ ነው ደላችን።
ፕሪምየር ሊጉ የዲ ኤስ ቲቪ ዘመን ላይ ማሸነፋቹ የተለየ ደስታ አለው ?
” አዎ። የተለየ ነው ብዬ የማስበው ካረጋገጥን በኃላ ማሸነፋችን። ያም ማለት የተለያዩ ሰዎች ይለቃሉ ጨዋታውን የሚባል ነገር ነበረ ። ይሄ የኛ ስራችን ነው። ካሸነፍን እናሸንፋለን። ከተሸነፍንም እንሸነፋለን። ጥረን ካልቻልን ለማሸነፍ ነበር የተጫወትነው እግዚአብሔር ይመስገን ተሳክቶልን አሸንፈናል።
በ20 ጎሎች ሙጂብ ቃሲም ሁለተኛ ኮከብ ጎል አግቢ ነው፣ ለሱ ካስ ለመስጠት ተነጋግራችሁ ነበር ?
“አዎ ። አሁን እየተቸገርንም ያለነው ሁሉም ሰው ለሙጂብ ላይ ነው ትኩረቱ። ለማቀበለም አልተመቸነም ግን ልንረዳው ብዙ እንሞክራለን። ያ ነገር ብዙ ያሰብነውን እያሳጣን ነው ያለው። ማለትም ብዙ ሰው ትኩረት እያደረገበት ስለሆነ ያንን ማድረግ አልቻልንም።
ለእሱ ለመስጠት እያሰበ ስላስቆጠራት ጎል
” አዎ። የዛሬውን ጎሉን አቀባዩ እኔ ሆኜ ሙጂብ ቢያገባ ደስ ይለኝ ነበር (በፈገግታ) “