የፋሲል ከነማን እግር ክለብ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት የ2013 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።
በ49 ነጥብ ሊጉን የሚመራው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ሻምፒዮና መሆኑን ያረጋገጠው በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው እና 35 ነጥብ ያለው የኢትዮጵያ ቡና ስፓርት ክለብ ዛሬ ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያለ ጎል በማጠናቁ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በቀሪዎቹ አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ እንኳ ቢችል የሚኖረው የ 12 ነጥብ ውጤት በመሆኑ እና ይህም ተደምር 47 ነጥብ በመሆኑ ፋሲል ከነማ ሻምፒዮና መሆኑ ተረጋግጧል። እንደሚታወሰው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከፋሲል ከነማ ጋር የአሸናፊዎች አሽናፊ ዋንጫ አግኝተዋል። በ በ1994 እና 1995 ዓ. ም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሊጉን ዋንጫ አሽናፊ ሆናል ።
የሻምፒዮኖቹ አሰልጣኝ ስዮም ከበደ ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ያደረጉትን ወሳኝ ጨዋታ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በቀጥታ ተከታትለው በመጨረሻም ደስታቸውን ከቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ ጋር በስታዲየሙ ሲገልፁም ተስተውሏል። የዐፄዎቹ ዋና አሠልጣኝ ስዩም ከበደ የደስታ ስሜታቸውን ለኢትዮ ኪክ በዚህ መልኩ ገልፀዋል።
” የቤትኪንግ ፕሪሜር ሊጉን ዋንጫ ክብር በመቀዳጀታችን ለፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ብዙ መስዋዕትነት ከፍለዋል። .ላለፉት ሁለት ዓመታትም ጫፍ እየደረሰን በተለያዩ ምክንያቶች አልተሳኩም። .እነሆም በዚህ ዓመት 4 ጨዋታዎች እየቀሩን ሻምፒናውን አሳክተነዋል። ታዲያ ለዚህ ሁሉ ተጠቃሸ የሆኑት እና ከጎናችን ሁሌም ያሉት ደጋፊዎች ናቸው።ለዕንቁ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎቻችንን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉ በታላቅ ደስታ አሰልጣኝ ስዮሥ ለኢትየ ኪክ ተናግረዋል
በቀጣይ ጨዋታዎች ፋሲል ስሊሚኖረው ለውጥ አሰልጣኝ ስዩም እንዳሉት ” ክብራችንን በጠበቀ መልኩ የሚመጣጠን ጨዋታ እንጫወታለን” በማለት ምላሽ መልስ ሰጥተዋል። ሻምፒዮና ከመሆናቸው ጋር የኮከብ አሰልጣኝችን አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ይቀዳጃሉ ለሚለው ጥያቄ ምን ትላለህ ? ” የኮከብ አሰልጣኝነት ለእኔ አንድ አሰልጣኝ የክለብን ከፍታ ጫፍ ካደረሰ ተያይዞ የሚመጣ ሽልማት ነው ” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል።