ዜናዎች

“ቡድናችንን አሸናፊ ለማድረግ በርትተን እየሰራን ነው፣ በቀጣይ ጨዋታዎችም ጠንክረን እንሰራለን ብዬ አስባለሁ “-ቸርነት ጉግሳ

በዘንድሮው የ2013 የቤትኪንግ ውድድር ላይ በችሎታቸው እና በፈጣን የኳስ ክዕሎቱ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን እያዝናኑ ካሉ ወጣት ተጨዋቾች መሀል የወላይታ ድቻው ቸርነት ጉግሳ አንዱ ነው።የጦና ንቦች ቸርነት ጉግሳ በመስመር በኩል በአብዛኛው የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮችን ለማለፍ የሚሰራቸው አብዶዎች ልዮ ናቸው። በተለይም በቡድኑ ውስጥ ከጎል አዳኙ እና ከአጥቂው ስንታየሁ ጋር ያላቸው ጥምረት የተሳካ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በዛው በቡድኑ ውስጥ ታላቅ ወንድሙ አንተነህ ጉግሳ የሚጫወት ሲሆን ሌላኛው ወንድሙ ሽመክት ጉግሰ በፋሲል ከነማ ይጫወታል ።በጥሩ አቋም ላይ ከሚገኘው የመስመር አጥቂ ቸርነት ጉግሳ ጋር ኢትዮኪክ አጭር ቆይታ አድርገናል።

ኢትዮኪክ : – ዘንድሮ የቸርነት ብቃቱ የተለየ ነው በማለት በርካቶች ስላንተ ይናገራሉ፤ አንተስ በዚህ ላይ የምትለኝ ይኖራል   ?
ቸርነት :- አዎ ..ማለት ፕሪምየር ሊጉን እየተላመድን አየመጣን ስለሆነ ፣ እኔም ያለኝ አቋምና ብቃቴ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻልኩ እየመጣው ነው ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮኪክ : – ከቡድን አንፃርስ ወላይታ ድቻ የዘንድሮ አቋም እንዴት ትገልፀዋለህ ?
ቸርነት :- አዎ ቡድናችን መጀመሪያ አካባቢ ጥሩ አልነበርንም። ከዛ በኃላ እየተሻሻልን መጥተናል። በተለይም ህብረታችንን አስተካከልን ። የሚሰጠንን ነገር በአግባቡ መተግበር በመቻላችን አሪፍ ላይ ነን ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮኪክ : – የቡድናቹ ጠንካራ ጎን በአንተ ዕይታ ምንድነው ትላለህ ?
ቸርነት :- የቡድናችን ጠንካራ ጎን ብዬ የማስበው ህብረታችን ነው። ስህተቶች ሲኖሩሞ እየተራረምን፣ እየተነጋገን በአጠቃላይ ህብረታችን ነው ብዪ አስባለሁ።
ኢትዮኪክ : – አሁን ሐዋሳ ነው ያላችሁት በቀሪ አምስት ጨዋታዎች የቸርነት አቋም እንዴት ሊሆን ይችላል ብለን እንጠብቅ ?
ቸርነት :- ያው ከፈጣሪ ጋር ያለኝን ነገር ማስቀጠል ነው የማስበው እኔ። ባለኝ ብቃት ላይ እጨመርኩ መሄድ ነው የምፈልገው።
ኢትዮኪክ : – ከወላይታ ድቻ ጋር ያለህ ኮንትራት መቼ ነው የሚያልቀው ?
ቸርነት :- ኮንትራቴ ዘንድሮ እጨርሳለሁ
ኢትዮኪክ : – ከዚህ በተያያዘ ቸርነት ያሰበው ነገር ካለ ?
ቸርነት :- እስካሁን ምንም ያሰብኩት ነገር የለም። ያው ውልን እስከምጨርስ ምንም የማስበው የለም። ውሌ ካለቀ በኃላ ነው መነጋገር የምንችለው።
ኢትዮኪክ : – አንዳንድ የሚባሉ ነገሮች አሉ ፣ በሊጉ የሚገኙ ክለቦች ገና ከአሁኑ አንተን የመጠየቅ ሂደቶች መጀመራቸው ይህ ምን ያህል እውነት ነው ?
ቸርነት :- አይ ምንም ነገር የለም። እኔም ያሸብኩትም ነገር የለም። አሁን ባለሁበት ክለቤ ቡድኔን አገልግዬ ጨርሼ ከዛ በኃላ ነው መነጋገር የምችለው።
ኢትዮኪክ : – ሌላው ቡድን ውስጥ አንተነህ አለ ፣ ከወንድም ጋር የሚሰጠው ደስታ ግለፅልኝ ?
ቸርነት :- አዎ …ያው ከወንድም ጋር መጫወት በጣም ነው ደስ የሚለው። ችግር ካለብሽ ችግርሽን ይነግርሻል ። ይህንን ችግር አስተካክል ይላል፣ያበረታታል በአጠቃላይ ከወንድም ጋር መጫወት በጣም ትልቅ ነገር ነው። በጣም ደስ ይላል።
ኢትዮኪክ : – ከአጥቂው ስንታየሁ ጋር ያለችሁ የቡድን ጥምረት ምን ይመስለኛል ?
ቸርነት :- አዎ …ከስንታየሁ ጋር ደስ የሚል ጥምረት ነው ያለኝ። አንደውም የአንድ ሰፈር ልጆችም ነን ስለዚህ ጥሩ ጥምረት አለን።
ኢትዮኪክ : – አንድ ሰፈር ልጆች ስትል የት አካባቢ ?
ቸርነት :- ማለት ሶዶ ነው ያደግነው። አንድ ሰፈር ነው ምንም እንኳ በጣም ትውውቅ ባይኖረንም ሰፈራችን አንድ አካባቢ ነው። በርግጥ እሱ እዚህ ትንሽ ይቀድመኛል ። ትውውቃችን በደንብ እዚህ ነው።
ኢትዮኪክ : – ስንታየሁን እና አንተነህ ጨምሮ የተወሰኑ ልጆች ከፊርማ ክፍያ ጋር ቅሬታ አቅርበው ነበር ሰሞኑን ፣ አንተም ነበርክበት ?
ቸርነት :- አይ እኔ አልነበርኩም።
ኢትዮኪክ : – አንተ ጋር ያለው ጥያቄ ሰላም ነው ?
ቸርነት :- አዎ በእኔ በኩል ሰላም ነው
ኢትዮኪክ : -በቀሪዎቹ አምስት ጨዋታዎች ላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊ ምን ይጨብቅ?
ቸርነት :- ቡድናችንን አሸናፊ ለማድረግ በርትተን እየሰራን ነው። በቀጣይ ጨዋታዎችም ጠንክረን እንሰራለን ብዬ አስባለሁ። ደጋፊዎቻችን ጥንካሬዎችን ናቸው። እነሱ ሲያበረታቱን በበለጠ ጥሩ ነገር የምንሰራው እና እነሱ በፅናት ያበረታቱን ነው የምለው።
ኢትዮኪክ : – ስለነበረን ቆይታ ቸርነትን እናመሠግናለን
ቸርነት :- እኔም እንግዳችሁ ስላረጋችሁኝ አመሠግናለሁ

One thought on ““ቡድናችንን አሸናፊ ለማድረግ በርትተን እየሰራን ነው፣ በቀጣይ ጨዋታዎችም ጠንክረን እንሰራለን ብዬ አስባለሁ “-ቸርነት ጉግሳ

Comments are closed.