ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የማራቶን ማጣሪያ መነሻውን ሰበታ ከተማ በማድረግ 35 ኪ.ሜ ማዘጋጀቱ ይታውሳል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፌዴሬሽኑ ያቅረብውን መሰፈርት በደብዳቤ በመቃወም ከቀናት በፊት ማሳወቁም እንዲሁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴም ትላንት ቀነኒሳ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ይሳተፋል በማለት አሳውቋል። በአንፃሩ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ዛሬው ከስፖርት ዞን የስፖርት ፕሮግራም ላይ ከጋዜጠኛ ሰኢድ ኪያር ጋር ረጅም ቆይታ አድርጎ በአገሩ መከፋቱንና ማዘኑን ጭምር ይፋ አድርጓል። አትሌቱ በዚሁ ዙሪያም ሊወስድ የነበረውን ውሳኔም አስመልክቶ የተናገረውን እንደሚከተለው ቀርቧል።
የሁልጊዜ ህልሙ ኦሎምፒክ ተሳትፎ በአህምሮ ምን ያህል ዝግጁ ነበረ ?
” እውነት ለመናገር ይሄ ውድድር ባለፈው አመት ነበር ይካሄዳል የተባለው። በ2020 ነገር ግን በኮቪድ ምክንያት ተራዝሟል። ሰለዚህ የ2020 ኦሎምፒክ ነውና የሚካሄደው። ከዛ አንፃር ከፍተኛ እምነት ነበረኝ እንደምሮጥ ምክንያቱም በወቅቱ ያስመዘገብኩት ሰአት እንደሚታወቀው ፌዴሬሽኑ ሰአት መደረግ ባደረገው ነበር። በዚህ መሰረት ውጥቴ በሚገባ ለኦሎምፒክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትልቅ ተስፋ ነበረኝ እንደምሰለፍ። እናም ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነበር። በቅርቡ ደግሞ ፌዴሬሽኑ ማጣሪያ ማድረግ አለብኝ ብሎ አሳውቆ ።ማጣሪያው ላይ እንደማልገባ ተቋውሞ አቅርቢያለሁ።”
በቅርቡ ተቋውሞውን ስለገለፀበት ምክንያት ? 35ኪሎ ሜትር ስለሆነ ነው ለምን እንደተቃወመ?
“አዎ ! ሲጀመር ኦሎምፒክ 2020 ላይ ነው ይደረጋል ተብሎ ባለን ሰአት ምርጫ ተደርጎ ነበር አምና። እንግዲህ ይሄ መስፈርት አዲስ ቸው የወጣው እና። ይሄ መሥፈርት ደግሞ አስቀድሞ አላሳወቁም ለአትሌቶቹ ። ውድድሩ በተቃረበበት ወቅት ነው የተናገሩት። ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው በሰአት ስለነበር በሰአት ነበር እኛም ሙሉ እምነት እና የምንጠብቀውም በሰአ ነው። አሁን ቀይረው ደግሞ ማጣሪያ አሉ። ይሄ አግባብ አይደለም። ማጣሪያ እንደገና ማጣራት አግባብ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ተናግሪያለሁ።
ያገኘዋቸውን የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ተነጋግሰናል ግን እንዲካሄድ አደረጉ። ሌላው ዋነኛ ነገር 35ኪሎሜትር የማራቶን ምርጫ ሊሆን አይችልም። ከዛም ባለፈ ወቅቱን የጠበቀ ነው ብዬ አላምንበትም ማጣሪያው በአጠቃላይ።
የፌዴሬሽኑ በኩል 35ኪሎሜት ምንም ችግር የለውም ይላሉ አንተ እንደ ማራቶን አትሌት የእንዴት ትመለከተዋለህ?
“ትክክለኛው የማራቶን ሩጫ የሚጀምረው እኮ ከ32 ኪሎሜትር በኃላ ነው። እንዴት ሆኖ ነው 35ኪሎሜትር የማራቶን መስፈርት የሚሆነው። ይሄ ውድድር እኮ ነው ። ትሬይኒንግ አይደለም አሁን ያደረጉት ውድድር ነው። ግን የእውነት የማራቶንን ርቀት ትክክለኛ የሚመዝን አይደለም። በአብዛኛው ጠንከር ያለ ፉክክር የሚደረገው ከ30 ፣ከ32 ኪሎ ሜትር በኃላ ነው። ስለዚህ 35 ኪሎሜትር የውድድሩ የመጨረሻ ማድረግ ውድድሩ የሚጀምረው ከዛ በኃላ ነው። ፉክክሩ የሚታየው የማራቶን ከዛ በኃላ ነው። እናም ይሄ ተገቢ አይደለም።
ሆቴል ከቡድኑ ጋር አለመቀመጡ በተመለከተ ?
” ሆቴል ያልነበርኩበት ምክንያት አሳውቂያለሁ። ለፌዴሬሽኑ የከፍተኛ አመራር አናግሬ። አንተ እቤትም ሆንክ ሆቴል ምንም ችግር የለውም። ትሬይኒንግ በአግባቡ ሥራ ችግር የለውም ተብዬ እንጂ በእምቢርኝነት አይደለም። ሆቴል የገባ እና ያልገባ ተብሎም የተቀመጠ መስፈርት የለም። “
ውድድሩ ከመደረጉ በፊት ነበርና ደብዳቤ ያቀረበው ፣ ወድድሩ ከተደረገ በኋላ የተሰማው ስሜት?
” ቅሬታዬን ያቀረብኩት አራት ቦታ ነበር። ማለት አራተኛ ሚዲያ አሳውቂያለሁ ። ከዛ በተጨማሪም ለኦሎምፒክ ኮሚቴ ቅሬታዬን አቅራቢያለሁ፣ ስፖርትኮሚሽን እና ፌዴሬሽን እና ይሄ አቅርቢያለሁ። አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታ አቅርቤ መልስ እጠብቅ ነበር። መልስ አልተሰጠኝም። አትሌቶቹ ስለሮጡ ስላልሮጡ በፊትና በኋላ ብዬ አላሰብኩም። እኔ ቅሬታዬን ያቀረብኩት አግባብ እንዳልሆነ እና ውድድር ከማድረጋቸው በፊት ነው። ውሳኔው ተለወጠ አልተለወጠም እኔ ማንንም ታርጌት አድረጌ አይደለም። ማንንም አትሌት ለመጉዳት አይደለም። አግባብ ባለው ለመብቱ ተከራክሮ በሚያስመርጥ መንገድ መሠለፍ ይፈልጋል። ስለዚህ ይሄ የአትሌቱ ጥፋት ነው ብዬ አልወስድም ። የአመራሩ ይሄንን ውሳኔ የሰጡ ሰዎች ነውና። ከዚህ አንፃር ይታወቅልኝ። ማንንም አትሌት ለመጉዳት አይደለም። ስለመብቴ ነው የተከራከርኩት ከዚህ በፊት ይደረግ በነበረው መሠረት ምረጡ ነው ያልኩት። አምና ምርጫ ባካሄዱት የተመረጡ ልጆች አሉ ከመራዘሙ በፊት Long list አለ ። ስለ መብቴ ነው እየተከራከሩ ያለሁት ማንንም ለመጉዳት /ለመጥቀም አይደለም።”
በደብዳቤውን ካሳወቅ በኃላ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኩል ቁጭ አድርጎ ያናገረህ ያወያህ አካል ይኖራል?
“ማንም የለም። ከዛ ባለፈ የአትሌቲክስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢያድግልኝ በስልክ ደውዬ ነበር ። አጋጣሚ እኔ ደብዳቤ ካስገባው በኃላ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተሰብስበው ነበር። የሰታው ውድድር ከመደረጉ በፊት ። ከዛ አቶ ቢያድግልኝ በስልክ አንተ ሮጠህ አራተኛ አምስተኛም ብትወጣ እናስገባለን። ግን ውድድሩ ውስጥ ብቻ ተሰለፍ ። አራተኛ ፤ አምስተኛም ብተወጣ ችግር የለውም ብለው በስልክ ነው ያሉኝ። ይሄ የሁሉንም የፌዴሬሽኑ ውስጥ ያሉትን አቋም 100 % ይወክላል ብዬ አላስብም። የግል አሳባቸውን ነው ያቀረቡት። እኔ ማጣሪያው ላይ አምኜበት ከገባው አንደኛ አምስተኛ ደረጃ ማስቀመጥ ያለባቸው አይመስለኝም። ተገቢም አይደለም። የተጠየኩት በአግባቡ በደብዳቤ መመለስ ነበረባቸው ። ወይም ደውለው ጠርተው ያለው ሁኔታ ይሄ ይሄ ነው ማለት ሲገባ የራሳቸውን ሃሳብ በስልክ ያወሩኝ። ይሄ ተገቢ አይደለም። ውድድር ካደረጉ አራተኛ አምስተኛ የሚታወቅ አይደለም። የመስፈርት ጥያቄ አይደለም። እኔ ብቃቴን አውቃለሁ። ጥያቄው የመብት እንጂ ውድድር ገብቶ የማለፍ ያለማፍ ጥያቄ አልነበረምና። እኔ ብቃቴ አውቃለሁ በዚህ መሠረት ነው የወሰንኩት “
ቀነኒሳ እ.ኤ.አ በ2016 በርዮ ኦሎምፒክ ላይ ተመሣሣይ የአካሄድ ችግር ምክንያት መሠለፍ እየፈለክ በውድድሩ ሳትሰልፍ ቀርተሃል ፣ አሁን ደግሞ ተመሳሳይ ችግር። በደብዳቤ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዕድሉን ካልሰጠኝ ሌሎች አማራጮች ያለው ምን ነበር ? ቀነኒሳ ተክፍቷል ለሀገር በሰራው ?
” እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዚህ ውድድር እንደምካፈል ነው። እንደምወዳር ነበር። የዛሬ አራት አመት ውስጥ ያመጣሁት ውጤት ያሳልፈኛል። ነገር ግን እንደ አዲስ መስፈርት እያወጡ ፣ ማራቶን ውድድር የሮጠ ብለው አዲስ መስፈርት ያሉት። ምክንያቱም የኔ በወቅታዊ ብቃቴ ወደ ውድድሩ ቀርቦም ይሁን ወይም በ6ወር ውስጥ ያስመዘገብኩት ውጤት ከፍተኛ ውጤት ነው። ወቅታዊ ብቃት አለኝ። ምናልባት አንድ ውድድር ነው፣ እነሱ አዲስ መስፈርት ያስቀመጡትን እንደማላሟላ እያወቁ አውቀው በሁለት በሶስት አመት ያስቀሩኝ ። ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ዘንድሮ ኦሎምፒክ እንዳልሳተፍ ሊያደርጉኝ ፣ አዎ ለምን አይከፋኝም በጣም ነው የከፋኝ። ብዙ ጥቅም የማገኝባቸውን ውድድሮች ትቼ ለሀገሬ በኦሎምፒክ ብሰልፍ ለእኔም ተጨማሪ ሜዳሊያ ባገኝ ለታሪክ ጥሩ ነው። ሀገሬንም በኦሎምፒክ መድረክ ብወክል ደስ ይለኛል። ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ከውድድር እንድቀር መደረጉ ተገቢ አይደለም። ከዛ አንፃር አንዳንድ ጊዜ በደል አትሌቶች ሲደርስባቸው ወይም ሀገራቸው ተቀጥታ ከሆነ ለምሳሌ በዶፒንግ ሊሆን ይችላል ፣ ወይም በሆነ ነገር ሲከለከሉ ብዙ አትሌቶች የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባንዲራ ወክለው ይወዳደራሉ። እናም ምናልባት ይሄ ህግ ምን ያህል ለእኔም ይስራ አይስራ አላውቀውም። ግን ከማናጀሬ ጋር ተነጋግሬ እንደውም የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባንዲራ ወክዬ በግሌ መሮጥ የሚል ሃሳብ ነበረኝ “
የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቀነኒሳ የእኔ አትሌት ነው መወዳደር ይችላል ብሏል በዚህ ላይ የተሰማው ስሜት
” እኔ ተቋውሞ ያደረኩት መሠለፍ አለብኝ ብዬ ነው። ቅሬታዬን ለኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ ለፌዴሬሽኑም ያቀረብኩት እንዲታይ ነው። ይሄንን ተቀባይነት አግኘቶ ከታየ። አዎ ኦሎምፒክ ወክዬ እወዳደራለሁ “
የአሁን ያለው ብቃቱ እና እንደ አበበ ቢቂላ ቶኪዮ ኦሎምፒክ ለማሸነፍ ያለው ዝግጁነት?
” አዎ ጥሩ ብቃት እና ጥሩ ጤንነት ላይ ነው ያለሁት። በቀሩት ጊዜያት በደንብ እራሴን አዘጋጅቼ ለሚዲያ ባሸንፍ ለራሴም ለሀገሬም ትልቅ ታሪክ ነው የሚሆነው “