የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ኢትዮዽያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ ከቀናት በፊት በሰበታ የ35 ኪ.ሜ ውድድር አዘጋጅቶ በሁለቱም ፆታ መምረጡ ይታወሳል።በአንፃሩ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያለው የአለም ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በውድድሩ ባለመሳተፉ በኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግልጽ ባልሆነ የውድድር መሥፈርት ከቶኪዮ ኦሎምፒክ የተገለለ መሥሎ የነበረ ቢመስልም ዛሬ ቀነኒሳ በቀለ በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንደሚሳተፉ ታውቋል።
የአኖካ አዲሱ ፕሬደዛንት ሆነው የተመረጡት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው መመረጣቸውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አያይዘው የቀነኒሳን ጉዳይ እንደተናገሩት አትሌት የመምረጥ ስልጣኑ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሆንም የመጨረሻው ውሳኔ ግን የእኛ ነው። ዋነኛ ፍላጎታችን የሀገራችንን ባንዲራ ከፍ የሚያደርግ ውጤት እንዲመዘገብ ነው። ተገቢ ባልሆኑ አሰራሮች ወቅታዊ ብቃታቸው ጥሩ ላይ የሚገኙ አትሌቶች ከውድድሩ እንዲቀሩ አንፈቅድም .ቀነኒሳ በቀለ በኦሎፒክ ይሳተፋል ፣ ቀነኒሳ ምንም ሳይረበሽ ልምምዱን ጠንክሮ ይሰራ በማለት ምክር አዘል መልክት ለሚዲያ ማስተላለፋቸው ተዘግቧል።
ውድድሩን ተሳተፍክ ማለት በእርግጠኝነት ታሸንፍለክ ማለት አይደለም በአሁኑ ሰአት ከአንተ የተሻሉ ልጆች አሉ በራስህ የምትተማመን ከሆነ ለምን ማጣሪያውን አልተወዳደርክም ከአንተይልቅ ለንደን ማራቶን ያሸነፈው ልጅ ቅድሚያ እድል ሊስጠው ይገባ በኒ ግምት አስልጣኝህ ያሉትን ልጆች በአላቸው አቃም መለየት አለብት አሁን ተመርጠው ያለፍት ልጆች ከአንተ የበለጠ የማራቶን ልምድ አላቸው አሁን ተመርጠው ያለፍት አትሊቶች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል