የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፓርት ክለብ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከቀናት በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ወሳኝ የሆኑት ተጨዋቾች
ጌታነህ ከበደ፣ አስቻለው ታመነ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ሙሉዓለም መስፍን ላይ አስደንጋጭ የዲሲፒሊን ግድፈት ፈፅመዋል በሚል በተጨዋቾቹ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ለክለቡ ድምፅ ” ለምንግዜውም ልሳን ጊዮርጊስ* የሬድዮ ፕሮግራም ላይ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አቶ አብነት እንደተናገሩት የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔው መተላለፉን እና የተፈፀመው ድርጊት በጅማ ፣ባህርዳር እና ድሬደዋም በተደጋገሚ በፎቾ እና ቪዲዮ የተደገፈ ነው በማለት በሬዲዮ ፕሮግራሙ መግለጫቸው ተናግረዋል።
በመሆኑም የክለቡን አምበል ጌታነህ ከበደን ፣ እንዲሁም ጠንካራ የክለቡ ተከላካይ አስቻለው ታመነ ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ሙሉዓለም መስፍንን ውላቸው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ማገዱን ይፋ ሲያረግ ከዚህ በተጨማሪም በተጨዋቾቹ ላይ የ 20 ሺ ብር ቅጣትም ክለቡ ማስተላለፉን አቶ አብነት በሬዲዮ ፕሮግራሙ መግለጫ ማሳወቃቸው አይዘነጋም። ይህ ውሳኔ ከተላለፈ በኃላም የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊዎች እና መላው የስፓርት ቤተሰብ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች እና አመለካከቶች እየሰጠም ይገኛል።
በስፓርት ቤተሰቡ ዘንድ በተጨዋችቹ ላይ የተወሰደው የስነምግባር ውሳኔ ጠንካራ ከመሆኑም አንፃር ተጨዋቾቹ የፈፀሙት ድርጊት በትክክል ለማወቅ መጓጓታቸው አልቀረም። በተጨማሪም ጌታነህ ከበደ እና አስቻለው ታመነ ብሔራዊ ቡድኑን የወከሉ ክመሆናቸው አንፃር በጉዳዩ ላይ ትኩረት ስቧል። በኢትዮኪክ በኩል የዋልያዎቹ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተከላካይ የሆነውን እና የስነምግባር ውሳኔ ካስተናገዱ ተጨዋቾች መሀል አስቻለው ታመነን አነጋግረናል ።
ኢትዮኪክ :- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የዲስፕሊን ግድፈት ፈፅማሃል ከተባሉ ተጨዋቾች ያንተም ስም አለ እና በዚህ ላይ ምን ትላለህ ?
አስቻለው :- በቅድሚያ በዚህ ጉዳይ ለእግር ኳስ ቤተሰቦች በፈፀምኩት የዲሲፕሊን ግድፈት ምክንያት በእጅጉ አዝናችሁብኛል። እኔም ፍጹም የጥፋተኝነት ስሜት የተሰማኝ እና የተፀፀትኩ መሆኔን እገልፃለሁ ። ዳግመኛም በእንደዚህ አይነት ጥፋት ላይ የማልገኝ ለመሆኑ ቃል እገባለው የሚለውን ነው የምለው።
ኢትዮኪክ :- ለስፓርት ቤተሰቡ ጉዳዪን ግልፅ ለማድረግ እና ጥፋታችሁን ማወቅ ለሚፈልጉ ምን አይነት ጥፋት አጥፍታችሁ ነው ይሄ ቅጣት ?
አስቻለው :- በርግጥ የተለየ ጥፋት ያደረግነው አልነበረም። እዚህ ደረጃ የሚያደርስም ጥፋት ነው ብይ በፍፁም በግሌ ያልጠበኩት ነው። ያደረግነው አምሽተን ስለገባን ብቻ ነው፣ ከዛ ውጭ የተለየ ምንም ነገር የለም ።
ኢትዮኪክ :- ፊልሞች እና ፎቶች የሚያነሳ ነበር የሚለው ምን የተለየ ነገር ቢሆን ነው?
አስቻለው :- ለእኔም ግልጽ አይደለም።
ኢትዮኪክ:- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ያለህ ውልህ መቼ ነው የሚጠናቀቀው ?
አስቻለው :- ውሌ የሚጠናቀቀው በዚህ ዓመት ነወ።
ኢትዮኪክ:- በፌስቡክህ ገፅህ ላይ ይቅርታ ጠይቀሃል ፣አሁንም ደግመህ በኢትዮኪክ በኩል የምትለው ?
አስቻለው :- በዚህ አጋጣሚም የምለው በፈፀምኩት ጥፋት ምክንያት ያዘናችሁብኝን መላውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ደጋፊዎች ፣ አመራሮች ፣ ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞችን ፣ እኔን አርዓያ ያደረጋችሁ የነገ ተስፋ የሆናችሁ ታዳጊ እግር ኳሰኞች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላትን እንዲሁም መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከልቤ ይቅርታ ለመጠየቅ እወዳለው ። ይህንን ይቅርታ የምጠይቀው የተወሰነብኝን ውሳኔ ለማስቀየር ወይም ለሌላ አላማ ሳይሆን ራሴን ከፀፀት ለማዳን መሆኑ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለው።
ኢትዮኪክ:- የይቅርታውን በፊስቡክ ለስፓርት ቤተሰቡ እንደጠየከው ለክለቡም ልከሃል ?
አስቻለው :- – ይቅርታው ለሁሉም የስፓርት ቤተሰብ ነው። ይህም በግሌ ያደረኩት ነው።
ኢትዮኪክ :- የጠየከው ይቅርታ ክለቡ የወሰነውን ውሳኔ ለማስለውጥ ነው ለሚሉ?
አስቻለው :- – አይ ፍጹም አይደለም። ይህንን ይቅርታ የምጠይቀው የተወሰነብኝን ውሳኔ ለማስቀየር ወይም ለሌላ አላማ ሳይሆን ራሴን ከፀፀት ለማዳን መሆኑ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለው።
we don’t know what kind of mistake have been done. if the mistake is high , the commitment of the board is really i appreciate. other players and clubs should be learn from st. gorge. all players are equal , what ever he is best player. it is good transfer opportunity to other clubs to the next summer. i want to see with Yared baye in Fasil FC