ዜናዎች

ክሻምፒዮኖቹ ጀርባ – ሦስቱ ድንቅ ተጨዋቾች ! !

የ2014 ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ከተቀላቀሉት ክለቦች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አንዱ ነው ። ቡድኑን ለሻምፒዮናት ካበቁት ተጨዋቾች መካከል ሦስቱን አናግረናል ። በቅድሚያ ግብ ጠባቂ ሳምሶን አሰፋ :-

 

 

ሳምሶን አሰፋ (ግብ ጠባቂ)

 

ሳምሶን አሰፋ የአዲስ አበባ ከተማ ግብ ጠባቂ ነው። ተወልዶ ያደረገው በድሬዳዋ ሲሆን የተጫወተባቸው ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ድሬዳዋ ከነማ ፣መብራት ሃይል፣ መተሃራ ስኳር አምስት ክለቦች ነው።

በፕሪሚየር ሊግ ለብዙ ዓመት ከመጫወት አንፃር ሱፐር ሊጉን  እንዴት አየኸው?
“ሱፐር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተጫወትኩት። በጣም ጨዋታ የሚችሉ ታዳጊዎች ተጨዋቾች ያሉበት እና ጥሩ ፉክክር ያለበት ነው። ጨዋታ አንብበው መቀየር የሚችሉ አሰልጣኞች ያሉበት ውድድር ነው። አዎ ፣ የፋሲሊቲ ችግሮች ይስተዋላል። ትኩረት የማይሰጡበት ሁኔታ እና የትጥቅ እና  ተያያዥ ችግሮች በጣም አለ ። አብዛኞቹ የክለቦች በአሰልጣኞች እና በተጨዋቾች ጥረት የቆሙት እንጂ ትኩረት የተነፈጋቸው ናቸው። በአንፃሩ ትኩረት ቢደረግላቸው በረካታ ለሀገር የሚበቁ አሰልጣኞች እና ተጨዋቾች የሚገኙበት ነው። በሚዲያ በኩል ከተወሰኑ ሜዲያዎች ውጭ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡትም አይደለም። በአጠቃላይ ግን ሱፐር ሊጉ የፋይናንስ ችግር ያለበት በወቅቱ ደሞዝ የማይከፈልበት፣ ያም ሆኖ በአሰልጣኞች እና በተጨዋቾች ጥረት ጥሩ እግር ኳስ የሚታይበት ውድድር ነው።
በ13 ጨዋታ በተከታታይ ጎል ያልተቆጠሰብህ  ምስጢሩ ምንድ ነው  ፣ በሮበርት ዶንጋራ በ14 ጨዋታ የተያዘ ሪከርድ ነው።  እሱ በፕሪሚየር ሊጉ ቢሆንም  ?
 ምንም ሚስጥር አልነበረውም። ነገር ግን ሚስጢር የነበረው መሥራት ነበር። ክለቡ ከዋና አሰልጣኝ እስማኤል እሰከ በረኛ አሰልጣኝ አሉ። የበረኛ አስልጣኙ እራሱ ተጨዋች ሆኖ ያሳለፈ ከመህኑ አንፃር አሁን ላይ የዘመናዊ ስልጠና እራሱን ያደበረ ልምድ ያለው ነው። እሱ የሚሰጠኝን ስልጠና በመሰራት የመጣ ብቃት ነወ። ሌላው በተከታታይ ክፍል ያሉ ልጆች ጎል እንዳይቆጠርብን በአጠቃላይ ቡድኑ ጎል እንዳይቆጠር የራሳቸውን ድርሻ በጋራ በመወጣታችን በ13 ጨዋታ ምንም ጎል አልተቆጠረብኝም። አሁን ቃለምልልስ እስካደረግነው ድረስ 20ጨዋታ ተጫውተናል። ከ20 ጨዋታዎች የገባብን 6 ነው። አንደኛው ዙር ላይ ነበር እሱ። ከዛ በኃላ ግን ከተወሰኑ ጨዋታዎች ጀምሮ ለተከታታይ 13 ጨዋታዎች ጎል አልተቆጠረብንም። ስለዚህ ይህ የሁሉም የቡድኑ የአሰልጣኞቹ ድንቅ ጥምረት ነው ከእኔ በተጨማሪም።
በተለያዮ አሰልጣኞች ሰልጥነሃል አሁን  የሚያሰለጥንህ  አሰልጣኝ እስማኤል የተለየ የሚያደርግው ?
እስማኤል የውድድሩ ጊዜ በጣም ማጠሩን አውቆ ሁሉም ነገር እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ አለማድረጉ በጣም ነው ያደነቁት። ምን ለማለት ፈልጌ ነው እስማኤል የተለየ አሰልጣኝ ነው። እኔ የምፈልገው ብቻ ሳይሆን ተጫዋቾች ምን ይፈልጋሉ የሚለውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አምብቦ እሱ ወደ ተጨዋቾች መጥቶ ተጨዋቾችን ወደ ራሱ ያደረገበት ጥበብ ለሌሎች አሰልጣኞችም ትምህርት ነው። ምናልባት እሱ የፈለገውን ብቻ ቢጥር ኖሮ በአጭር ጊዜ ሻምፒዮና አንሆንም። ይህን ጥልቅ በአጭር ጊዜ ውጤታማ የመሆን የእግር ኳስ አሰራር አካሄድ ፌዴሬሽኑና ሌሎችም ሊማሩት ይገባል። የሄደበት መንገድ በጣም የተለየ ነው ።አዲስ ልጆችን ና ልምድ የሌላቸውን ከተወሰኑ ልምድ ካላቸው ጋር አጣምሮ በአጭር ጊዜ ሶስት እና አራት ጨዋታ እየቀረው ውጤታማ ስራ የሰራ አሰልጣኝ ነው ። በተጨማሪም ቡድኑ ያገባነው የገባብን በጥቅሉ ማንም በአጭር ጊዜ ውጤታማ ይሆናል ብሎ አያስብም። በጣም ነው በግሌ ያደነቁት ይን ሰኬቱን ፌዴሬሽኑ የተለየ ስልጠና ቢሰጥና ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ አሰልጣኝ ነው።በተጨማሪም ምክትል አሰልጣኝ ደምስም ፣የበረኛ አሰልጣኝ መሠረትም ሊመሰገኑ ይገባል። በአጭሩ እስማኤል የሚደነቅ እና ለወጣት አሰልጣኞች ሞራልና ትምህርት የሚሆን ነው። በግሌ በጣም በጣም አድናቆቴ ነው።
በመጨረሻ ከዚህ ጉዳይ ጋር ባይገናኝም ረጅም ዓመት በአምበልነት ያገለገልክበት ድሬዳዋ ከተማ ጋር የተለያየህበትን ልትነግረኝ ትችላለህ ?
በዚህ ጉዳይ ምንም አስተያየት መስጠት አልፈልግም። አሁን ላይ ያለውን ደስታዬን የሚያጠፋ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ምንም ማለትን አልፈልግም። ፈጣሪ የድሬዳዋ ከተማ መልካም ነገር ብቻ ያሰማኝ ሌላው ባልናገረው እመርጣለሁ። ግን  የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾች ማመስገን እፈልጋለሁ። እንደ ታላቅ ወንድም ነው የሚያኙኝ፣ የሚያዳምጡኝ በመቀጠል የአሰልጣኞች ክፍል እንደ ወንድም ተከባብረን ደስ የሚል ጊዜም በማሳለፋችን እንኳን ደስ ያለችሁ እላለሁ። የክለቡ ኃላፊዎች ማመስገን እፈልጋለሁ።

ከድር አዪብ (አምበል )

የአዲስ አበባ ከተማ አምበል ነው። ተወልዶ ያደገው ድሬዳዋ ከተማ ሲሆን ኳስ የጀመረው ከድሬዳዋ ፖሊስ ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም የስልጤ ዞን ተጫውቶ አሳልፏል። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ጥሩ ጊዜ እያሰለፈ ያለ ተጨዋች ነው።

ለሻምፒዮንነት ያበቃችሁ ሚስጥር ?
 ” እኔ በዋነኝነት ለዚህ ያበቃን ብዪ የማስበው እኛ ውሰጥ ያለው አንድነት ታጋይነት ሲሆን አብዛኛው ተጨዋቾች ታዳጊዎች ሲሆኑ እኛ ልምድ ያለነው ደግሞ እነሱን ማኔጅ በማድረግ አብረን በአንድነት እርስ በርስ ፍቅርና መከባበር  መሥራታችን ነው። አሁንም ከአሰልጣኞቹ ጋር ጠንክረን የሚሰጡንን ነገር ጠንክረን በመስራታችን ሻምፒዮና ሆነናል።”
ቤትኪንግ ገብታችⷛላ ምን ታስባላችሁ የሚቀጥለው ዓመት ?
” እኛ የቻልነውን አድረገን ቡድኑ ለዚህ በቅቷል ።ቡድኑ የመድናዋ የትልቋ ከተማ ቡድን ነው። እንደሌሎቹ ቡድኖች ትልቅ ደረጃውን ማስቀጠል ነው። ያንን ማድረግ የምንችለው ዛሬ የያዝነውን መልካም ጅማሮ ሁሉም የክለቡ አመራሮች የየራሱን ድርሻ በጋራ ስንወጣ ነውና ትኩረት መስጠት እንዳለባችው ።   ቡድኑ የመድናዋ የትልቋ ከተማ ቡድን ነው ፣ታላቅ ቡድን በጋራ ታላቅ እናድርግ ነው የምለው። በመጨረሻ ማመሰገን የምፈልገው አሰልጣኞቻችን ነው። አሰልጣኞቻችን በብዙ ችግሮች ጠንካራ ሆነው ይህንን ውጤቶች እንድናመጣ በጣም ብዙ ነገር አድርገዋል፣  ያንን ማመስገን እፈልጋለሁ። እንዲሁም ተጨዋቾችን ማመስገን እፈልጋለሁ። በአብዛኞቹ ታዳጊዎች ናቸው እኛ የምንላቸውን የመቀበል አቅማቸው ከፍተኛ ነበር እና እሺ እያሉ ወደምንፈልገው ውጤት እንድንመጣ ያሳደረ እነሱን ማመስገን እፈልጋለሁ። ሌላው ደግሞ የቡድኑ አመራሮች ከጎናችን ስለነበሩ አመሰግናለሁ።

ሮቤል ግርማ (ተከላካይ )

የአዲስ አበባ ከተማ የግራ ተከላካይ ነው። ከ20 ጨዋታዎች 17 ጨዋታ ተጫውቷል። ሁለት ጨዋታ ይቀራቸዋል። ሦስቱን በጉዳት አልተሳተፉም ነበረ። ያደገው መብራት ሃይል ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲገባ የቲሙ አባል ነበረ።
በከፍተኛ ሊግ ተሳትፎአችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ቡድንን ደግም እንዲመለስ እናንተ ምክንያት ናቹ ይባላል ?
 ” በመጀመሪያ ለሻምፒዮና ያበቃን ብዬ የማስበው አብዛኞቹ ተጨዋቾች ወጣት ከመሆናቸው አንፃር የተባሉትን ከመሥራት እና እኛም ካለን ልምድ አንፃር የምንላቸውን የመቀበል አቅማቸው በጣም ጠንካራ ነበር። በጣም የበለጠ ደግሞ አሰልጣኞቻችን የሚሰጡንን ነገር የመቀበላችን እንዲሁም የቡድን ፍቅር እና ህብረቱ ይመስለኛል ለዛ ይመስለኛል ሻምፒዮና የሆነው። “
ለሻምፒዮናነት ያበቃችሁ ምን ነበር ጠንካራ ጎን ?
 “ሚስጥር ብዬ የማስበው አንደኛው እና ትልቁ ሚስጥር ከኃላችን ያለው ሳሚ በመሆኑ እርግጠኞች ነን። ሌላው የቡድናችን የማጥቃትና የመከላከል አቅም በጣም ጠንካራ በመሆኑ ቶሎ ተደራጅተን ሰው ሜዳ በመገኘታችን ሰው ሜዳ በመገኘታችን ነው። ከኃላ ሳሚ በመሆኑ የበለጠ በራስ መተማመናችን የዛን ያህል ስለነበር ለዛ ነው ብዬ አስባለሁ “
መጨረሻ ማለት የምትፈልገው ?
 “በመጨረሻ የምለው   የአሰልጣኞች የክፍል በተለይ ዋናው አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር ማመስገን እፈልጋለሁ ፣  አንዳንዴ ሰዎች የሚሰጡሽ ስም አለ እናም ከዛ ስም አውጥቶሽ የተሻለ ቦታ የሚያደርግ ሰው ነው። ለምሳሌ እኔ በግሌ ብዙ ነገሮች በዲሲፕሊን ተብዬ ብዙ ያልሆኑ ስሞች ተሰጥቶኝ ነበር። ነገር እስማኤል ያንን አሜኔታ ወስዶ እዚህ ደረጃ እንደደርስና ፣ ስራዪን እንዳውቅ ስላደረገኝ እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ። ከዛ በመቀጠል ሁሌም ከጎኔ ሆና ብርታት የሆነችኝን እናቴ አሰለፍ ያለሽ ዕድሜና ጤና ይስጥሽ አመሠግንሻለሁ ። በአጠቃላይ የአሰልጣኞች ክፍል አመሠግናለሁ።