ዜናዎች

” አብዛኞቹ ዋናው ቡድን ላይ ያሉት ተጨዋቾች ጓደኞቹ ሲሆኑ፤ ሙሉ ቡድኑ ሃዘን እና ድንጋጤ ላይ ይገኛል: ልጆቹን አፅናንተን ለጨዋታ ዝግጁ እናደረጋቸዋለን ” ➖ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ አዳማ ላይ በመካሄድ ይገኛል። ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ጊዜ በቀረው እና በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር አሰዛኝ ክሰተት ትላናት ምሽቱን ተከስቷል።የሐዋሳ ተስፋ ቡድን ግብ ጠባቂ አቤል አያናው ባልታወቁ ሰዎች ትላናት ምሽቱን ህይወቱ ማለፉ ታውቋል። ኢትዮኪክ ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት በፓሊስ በማጣራት ላይ እንደሆነ እና ለጊዜው የተጣራ መረጃ እንደሌለ ተጠቁሟል።በአንፃሩ አስዛኙ መረጃ ከተሰማ በኋላ በድሬደዋ ላይ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ የማሸነፍ መንፈስ ላይ የሚገኘው የሐዋሳ ዋናው ቡድን ተጨዋቾች መዳናገጣቸው እና ክፉኛ መረበሻቸው ተሰምቷል።
በተለይ በድንገት ህይወቱ ያለፈው ተጨዋች አቤል በድሬዳዋ ከሚገኘው ቡድን አብዛኞቹ ተጨዋቾች ጓደኞቹ መሆናቸው ሲሰማ ይህን ሀዘን በቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ሀዘን መፍጠሩ ተሰምቷል። ይህንንም ለማረጋጋት አሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረት እና ረዳቶቻቸው አፋጣኝ ውሳኔ መውሰዳቸው ተሰምቷል።
በድሬዳዋ የሚገኘው የሐዋሳ ዋናው ቡድን ተጨዋቾች ድንጋጤ እና ሀዘንን በተመለከተ እንዲሁም ቡድኑን ለማረጋጋት እየወሰዱ ስላለው ተግባር ለአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ኢትዮኪክ ጠይቀን ነበር ። አሰልጣኝ ሙልጌታ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተውናል።
” በመጀመሪያ ደረጃ የሰማነው ነገር በጣም ከባድ እና አሳዛኝ ነው። እኛም እዚህ ድሬዳዋ ሆነን ነው የሰማነው። ገና ምንም የተጣራም መረጃ የለም። ተጨዋቹ የተስፋ ቡድኑ እና ወደፊት ተስፋ የተጣለበት ነበር ። በጣም ያሳዝናል ሁኔታው። እዚህ ደግሞ ብዙ ጓደኞች አሉት ፤ ወጣቶቹ አብዛኞቹ ዋናው ቡድን ላይ ያሉት ተጨዋቾች ጓደኞቹ ሲሆኑ፤ በደንብ ይተዋወቃሉ። እናም ሙሉ ቡድኑ ሀዘን እና ድንጋጤ ላይ ይገኛል። እኛም እንደ ባለሙያ ጊዜ ሰጥተናቸዋል። ጨዋታችን ከነገ በስቲያ ስለሚሆን ልጆቹን አፅናንተን ለጨዋታ ዝግጁ እናደረጋቸዋለን። ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ሙሉ ቡድኑ ተሰምቷቸዋል” በማለት አሰልጣኙ ከተናገሩ በኋላ
ድሬዳዋ ላይ ቡድናሁ ጥሩ አቋም ላይ ነበር። አሁን ከተከሰተው ሃዘንም ጋር ሃዋሳ ከመሄዳችሁ በፊት የመጨረሻ ጨዋታችሁን መገመት ይቻላል ለሚለው ?
” ምንም የተለየ ዝግጁት እያደረግን አልነበረም። እስካሁን ጥሩ ውጤት ነበርን አሁንም እናስቀጥላለን። በተጨዋቹ ሞት ሀዘኑ ሙሉ ድንጋጤን ፈጥሯል በቲሙ ውስጥ። ልጆቹን በማረጋገት ቀጣይ ጨዋታውን ውጤታችንን እናስቀጥላለን። ” በማለት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ለኢትዮ ኪክ ተናግረዋል።