ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አስካር እስከ 2022 በኖርዌ ዋናው ሊግ ለመጫወት ውሉን አራዝሟል !

 
በኖርዌ ዋናው ሊግ ለክሪስቲያሱድ እየተጫወተ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሚን አስካር   እ.ኤ.አ እሰከ ፈረንጆቹ  2022 ለመጫወት  ውሉን ማራዘሙን የኖርዌው ክለብ አስታውቋል። በኖርዌ ለዋናው ሊግ ‘Eliteserien’ ተወዳዳሪ ለነበረው  ክለብ እጅግ ሲበዛ ተወዳጅ የነበረው ትውለደ ኢትዮጵያዊው አሚን ሱሊማን አስካር የኖርዌይ ዋናው ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ክሪስቲያሱድ  ክ2019 ዓ.ም  ከተቀላቀለ በኃላ እስከ 2022  ዓ.ም ለመጫወት የሚያሰችለወን   ውሉን ማራዘሙን  ክለቡ አስታውቋል  ።
ክለቡ እንዳስታወቀው የ35 አመቱ ሁለገብ ተጨዋች አሚን አስካር ቤተሰቡ በተቻለ ፍጥነት ወደ ሚኖርባት ከተማ Kristiansund ይመጣሉ ፣ እነሱም እዚህ ይኖራሉ  እነሱ  ወደ Kristiansund ውስጥ ባይመጡ ኖሮ  እዚህ መቆየት አይቻልም ነበር  ስለዚህ ይህ አስደሳች ዜና ነው በማለት ክለቡ አስታውቋል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አስካር ከኖርዌያዊቷ የሴት ጓደኛው የ7አመት ወንድ ልጅ እና የ4 አመት የሴት ልጅ አባትም ነው።