የጅማ አባጅፋሩ ተመስገን ደረሰ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ፈጣኗን ጎል አስቆጥሯል። ተመስገን በሊጉ ስድስት ጎሎችያስቆጠረ ሲሆን የዛሬዋን ጨምሮ ሁለት ጎሎች ፈጣን ጎሎች ሆነው ተመዝግበዋል። ተመስገን ከጨዋታ በኃላ ከሱፐር ስፓርት ቆይታ አድርጓል።
ዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድኑን ወጥ ያልሆነ ውጤት ይታይበታል። ስለዛሬው ጨዋታ ያለው አመለካከት?
” ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እንደመጫወታችን ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር። እኛም ግምት ሰጥተን ነው የገባነው ሜዳ ። እነሱ ተጭነው እንደሚጫወቱ እርግጠኛ ነበርን እኛም እነሱን ተጭነን ለመጫወት ነበር። ያለን አማራጭ የማሸንፍ ነው የመሸነፍ አልነበረም። አቻ መውጣቱ ምንም ጥቅም የለውም ለኛ።እና አቻ በመውጣታችን ደስተኛ ነኝ።
ጎሉ ፈጣን ነበርና አስባችሁበት ነበር ?
” እኔ አላወራሁም ከእነሱ ጋር። ግን እነሱ አውርተውታልና ፕሪንስ ቀጥታ ወደ ቦክስ ላከው ቦኮስ ውሰጥ መገኘት ነበረብኝ እና ኳሱ ተቆጣጠርኩት ከዛ ሃይል የነበረው ኳስ ስለነበር ገብቷል።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጅማአባጅፋር እንተርፋለን ብላችሁ ታስባላችሁ ?
” ዘንድሮ እንተርፋለን፣ አንተርፍምም ለማለት ይከብዳል ፤ ኳስ ነውና ምን እንደሚፈጠር አብረን እናያለን። እኛ የተሻለ ነገር እያደርግ ነው የመጣንበት መንገድ ከባድ ነው። እርግጠኛ ነኝ የሆነ ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ በመጨረሻ ላይ።
የአሰልጣኞች መለዋወጥ ለቡድኑ ጫና ፈጥሮበታል ?
አዎ ከባድ ነው ። ሁሉም የራሱን የጨዋታ ስልት ይዞ ነው የሚመጣው ። አሁን ያለው ጥሩ ይመስለኛል። ለእኛ ጥሩ ነው። የተሻለ ነገር ከአንደኛው ዙር በተሻለ እያየን ነው እና አሁን ላይ ጥሩ ነው ባይ ነኝ ።
ጎሏን ለማን ትሁን ?
” ለቤተሰቦቼ ይሁንልኝ”