ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ለቀጣይ ጨዋታ ሲዳማ ቡና አሸንፈን ሦስት ነጥብ ለማምጣት ጥረት እናደርጋለን “ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ (ድሬዳዋ ከተማ)

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ  የድሬደዋ ከተማ ከባህርዳር አቻው ጋር አንድ ለ አንድ ተለያይተዋል። ከጨዋታው በኃላ የድሬደዋው አሰልጣኝ
ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ    ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የሚገባውን ውጤት አግኝቷል ቡድንህ ?
ጥሩ ነበርን። ባህርዳር ከነማ ያው ኳስን መስርቶ አድርጎ ነው ሚጫወተው። ግን ሜዳቸው ላይም ብዙ ይቆያሉ። ስለዚል እኛ በመልሶ ማጥቃት ጎል የማጎባት ዕድል ፈጥረን ነበር ፣ የፍፁም ቅጣት ምትም አግኝተን ነበር  አልተጠቀምንበትም እንጂ ። እንደዛሬው ጨዋታ ግን ማሸነፍ ይገባን ነበር።  ከባህርዳር ከነማ  በተሻለ ውጤቱ ይገባን ነበር።
ስለ ጨዋታው እና የቡድኑ ተነሳሽነት
አዎ….. አኛ ያለንበት ቦታ ያቃጥላል ።በጣም አያስተኛም። ለማሸነፍ ፤ ቶሎ ቶሎ መስራት ያስፈልጋል። ያለነው በወራጅ ቀጠና ነው ። መተኛት ያስፈልጋል። በተገኘው አጋጣሚ ሶስት ነጥብ በማግኘት በሊጉ መቆየት ያስፈልጋል። አጠቃላይ እንዳየው የቡድኑ ስሜት ነው።
የብድኑ ችግሩ ምንድነው ለሚለው ?
ትንሸ ቡድናችን ጥራት ይፈልጋል። እንደነ ጁንያስ ቢኖር ጥሩ ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ የተሻለ ነው። ሁሌ እንደምለውየልጆቹ ብቃት እና ያለንበት ሁኔታ ተመሳሳይ አይደለም፤ ሁልጊዜም እንደማነሳው ነው ።ስለዚህ አሁንም ማሸነፍ እንፈልጋለን ። አሁንም ለቀጣይ ጨዋታ ሲዳማ ቡና አሸንፈን ሦስት ለማምጣት ጥረት እናደርጋለ።
ውጤቱ ተገቢ ትላለህ ?
የፍፁም ቅጣት ምቱ ከባህርዳር በተሻለ ለእኛ ይገባን ነበር።  ግን የተጫዋቾቹ ብቃት እና ያለንበት ደረጃ አንድ አይደለም። ስለዚህ ማሸነፍ እንፈልጋለን፤ በቀጣዩ የሲዳማ ጨዋታም ውጤት ለማምጣት ጥረት እናደርጋለን።