ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ከቡድኑ ጋር ሶስተኛ ጨዋታዬ ነው ፣ዛሬ ለማሸነፍ ነበር አቻ ለመውጣት ሳይሆን ያንንም አሳክተነዋል። ” ➖ዑመድ ኡክሪ

ንደሚታወቀው ዑመድ በግብፅ ሊግ በአል ሂታድ አሌክሳንደርያ :፣ ኤን ፒ ፒ ፣ ኤል ኤታንግ ፣ ሶሞኦ እና አስዋን በመጫወት በቁጥር አምስት የሚደርሱ ክለቦች በመጫወት ቀዳሚ ያደርገዋል ። ዑመድ ኡክሪ ከግብፁ ሊግ የመጨረሻ ክለቡ አስዋን ወደ አገሩ ተመልሶ በሀዲያ ሆሳዕና እየተጫወተ ይገኛል።ከዛሬው ጨዋታ በኃላ ዑመድ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ከግብፅ መልስ ሊጉን እንዴት አገኘኸው ?
” ሊጉ ከሞላ ጎደል አሪፍ ነው። እስካሁን አሪፍ ነው እየተራመድኩት ነው …”
በድሬዳዋ ሁለተኛ ጨዋታቸው አስመልክቶ
” ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻልን ነው። ያለውን ደረጃ ለማስጨበቅ ጥሩ ነገር እያደረግን ነው። ለዚሀ ነበር በዛሬ እንቅስቃሴ ለማሸነፍ ነበር አቻ ለመውጣት ሳይሆን ያንንም አሳክተነዋል።
ጎል ከማስቆጠርና ከማቀበል የሚመርጠው
” ሁለቱም ደስ ይለኛል። ማስቆጠሩ ደስ ይለኛል ግን ደግሞ ማቀበሉም ደስ ይላል’
የዛሬው የጨዋታ እንቅስቃሴ በቀጣይ የሚሰጠው በራስ መተማመን ይኖራል?
” በጣም በጣም …ገና አሁን ከቡድኑ ጋር ሶስተኛ ጨዋታዬ ነው።ከጨዋታ ጨዋታ ጥሩ ነገር ለማሳየት እጥራለሁ “
በDSTV ጨዋታው መተላለፍ መቻሉን ?
” ትልቅ ነገር ነው ። በDSTV መተላለፉ ለእኛ ተጨዋቾች እገዛ አለውና በጣም አሪፍ ነው።
ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመመለስ ፍላጎት?
” አብረን የምናየው ይሆናል (በፈገግታ)