ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

➖◾ የቤትኪንግ ሊግ – የድሬደዋ እውነታዎች ◾➖

⚽ ➖የ18ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ በሦስት ቀናት ጨዋታዎች በአጠቃላይ 12 ጎሎች ተቆጥረዋል። የኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱ ሪከርድ ለመስበር የኢትዮዽያ ቡናው አቡበከር ናስር 22 አሰቆጥሮ  ሶስት ጎሎች ቀርተውታል።
⚽➖በ18ኛው ሳምንት ፈጣኑ ጎል ሆኖ የተመዘገበው ሃዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር 1ለ1 አቻ በወጡበት ጨዋታ የጅማአባጅፋሩ ተመስገን ደረሰ ከእረፍት መልስ ፈጣኗ ጎል አስቆጥሯል።
⚽➖በ18ኛው ሳምንት ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ወጣቱ የጅማ አባጅፋር ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ የታየበት ሲሆን  ሃዋሳ ከ ጅማ አባጅፋር ባደረጉት ጨዋት ዒላማቸውን የተጠበቁ እና በትክክል ጎል ሊሆኑ የሚችሉ የጎል ዕድሎችን ግብጠባቂው አቡበከር ኑሪ አድኗል።
⚽➖የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ምሽት ጨዋታዎች በድሬደዋ ስታዲየም በ17ኛው ሳምንት ተጀምሮ በተሳካ መልኩ በመካሄድ ላይ ነው። ከመብራት ጋር የነበረው የDSTV የቀጥታ ስርጭት ችግርም አሁን ላይ ተቀርፎ ጨዋታዎቹ በሱፐርስፖርት መታየት ቀጥለዋል። እንደሚታወሰው DSTV በቅድሚያ በነበረው ህጋዊ ስምምነቱ በቀጥታ ስርጭቱ 60 ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ የነበረው ሂደት ተለውጦ እስካሁን ከ90 በላይ የቤትኪንግ ጨዋታዎች መተላለፍ ችለዋል።
⚽➖በድሬደዋ ኮቪድ እና የቡድኖች የምርመራ ውጤት አነጋጋሪነቱን ቀጥሏል። በተለይም ደግሞ የቡድኖች ውጤት ለምን ከሁለቱ ተቋማት የተለያዩ ሆነ የሚለው ምላሽ አላገኘም። ክለቦች በድሬዳዋ የምርመራ ውጤታቸው ኮቪድ አለባችሁ ተብለው በአለማያ ዮኒቨርስቲ ነፃ ናችሁ የሚባሉ ግን በርክተዋል።
⚽➖ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በትላንቱ ጨዋታ በመጨረሻ ሰአት ስታዲየም ከደረሱ በኃላ ወደ ሆቴል እንዲመለስ ተደርጓል። ከኮቪዲ ጋር በተያያዘ አሰልጣኛቸውን በመጨረሻ ሰአት የተለዮት ፋሲል ከነማዎች በቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እተየመሩ ከባህርዳር ከተማ ጋር ተጫውተው 0 ለ 0 አቻ ወጥተዋል። አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የምርመራው ውጤት ትክክል አይደለም ሲሉም የምርምራ ውጤቱን ተቃውመዋል።
⚽➖ የወርሀዊ ደሞዝ እና የፊርማ ክፍያ ካልተከፈለን ወደ ድሬዳዋ አንጓዝም ብለው የነበሩት የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች የ18ኛው የመጨረሻ ጨዋታቸው ሊካሄድ ሰአታት ሲቀረው ከኃላፊዎች ውይይት አድርገው ለጨዋታው ድሬ ደርሰዋል። ምሽት በ1:00 ሰዓት በድኑ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይቷል።
⚽➖ በ18 ኛው ሳምንት የሃዋሳ ከተማው አሰልጣኝ የሙሉጌታ ምህረት ደስታ አገላገፅ ብዙዎችን ፈገግ ያሰኘ ነበር ። በተለምዶ አሰልጣኝ ሙሉጌታ በዝመተኛነቱ ይታወቅ
ቡድኑ በጅማአባጅፋር 1 ለ 0 ሲመራ ቆይቶ ጨዋታው መጠናቀቅ አካባቢ ውብሸት አለማየሁ የአቻነቷን ጎል ሲያስቆጥር ደስታውን ሁለት የውሃ ላስኪቶችን በመወርወር ገልጿል።