ዜናዎች

ሽመልስ በቀለ ሀገራዊ ግዴታውን አጠናቆ ነገ ወደ ግብፅ ይጓዛል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ የአማካይ ክፍል ተጨዋች እና በዘንድሮው በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በስድስት ጎሎች ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎቹ በሶስት ጎሎች ርቆ በአራተኛ ጀረጃ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ከብሔራዊ ቡድኑ ግዳታና ከሳምንት እረፍት በኃላ ነገ ወደ ግብፅ ክለቡ ይጓዛል።
በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ጥሩ አቋም ይዞ ለተከታታይ አመታት በአማካይ ቦታ በስኬታማነት የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ በዘንድሮው የግብፅ ሊግ የተሻለ ብቃትም ላይ ይገኛል።
በተለይም በግብፅ ሊግ ምስር ኤል ማካሳ ከተደጋጋሚ ከሽንፈት እንዲወጣ ኢትዮጵያዊው አማካይ ትልቁን ሚና ተወጥቷል። ቡድኑ በሶስት ተከታይ ጨዋታዎች የማሸነፊያውን እና ብቸኛው ጎል በማስቆጠር ምስር ኤል ማካሳ በሁለት ጨዋታዎች 6 ነጥብ  በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡ እንዲሻሻል አስችሏል።  እንዲሁም በሌላኛው ጨዋታም ሽመልስ የጨዋታውን ቀዳሚ ጎል አስቆጥሮ የቡደን አጋሮቹ በተጨማሪ ሶስት ጎሎች እና  ሶስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት አስችለዋል።
በተመሳሳይ ሽመልስ በቀለ በክለብ ዘንድሮ የነበረው ድንቅ ብቃት በብሔራዊ ቡድኑም ተግባራዊ ሆኖም ታይቷል። ሽመልስ በቀለ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማዳጋስካር ላይ አስገራሚ አራተኛውን ጎል በማስቆጠሩም ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተደጋጋሚ ሃሣቡን አሳክቷል።  በግብፅ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወተው ሽመልስ ሀገራዊ ግዳታውን  እና ከሳምንት እረፍት በኃላ ነገ ወደ ግብፅ ይጓዛል። በደረጃ ሰንጠረዡ በ7ኛ ደረጃ የሚገኘው የሽመልስ ክለብ ምስር ኤል ማካሳ ዛሬ ምሽት በ18ኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ፒራሚድን በሜዳው ይገጥማል።