ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ዋንጫው ባይሳካም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውስጥ ብንገባ ደስ ይለኛል “- በረከት ወልዴ ( ወላይታ ድቻ )

ወላይታ ድቻ የ18ኛ ሳምንት ውጤቱን ድሬደዋ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ በድል አጠናቋል።በዛሬው ጨዋታ ለወላይታ ድቻ ከተቆጠሩት ጎሎች የመጨረሻዋን እና ወሳኟን ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ወጣቱ የአማካኝ ተጨዋች በረከት ወልዴ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
የዛሬውን ጨዋታ በተመለከተ
“አረፍ ነበረ። ውጤቱ ስለሚያስፈልገን እና እነሱም ወደ ላይ ከፍ እንዳይሉ እና ለእኛም ውጤቱ አስፈላጊ ነበር። ስለዚህ 6 ነጥብ አግኝተናል ብዪ ነው የማስበው ከጨዋታው ክብደት አንፃር።
በዛሬው ጨዋታ ወሳኝ የሜዳ ላይ ተግባሩ
” ዛሬ በነበረው ጨዋታ የተሰጠኝ ኃላፊነት እንዳጠቃ ነበረ።ኳስ በስነስርዓት እንዳደራጅ እና እንዳጠቃ ነበር የተነገረኝ ። ያንን በጥቂቱ አድርጊያለሁ ብዬ አስባለሁ።
ከቡደኑ ጋር የዘንድሮ ዕቅዱ
” ዋንጫው ባይሴካም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ብንገባ እና ብንጨረስ ደስ ይለኛል በራሴ ። እንደዛ አስበን እየሰራን ያለነው።